በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ክፍያ ተጀመረ


በትግራይ ክልል የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ክፍያ ተጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:19 0:00

በትግራይ ክልል የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ክፍያ ተጀመረ

የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ተከትሎ፣ ከ2013 ዓ.ም. ሰኔ ወር በኋላ፣ በትግራይ ክልል ተቋርጦ የቆየውን የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ መክፈል መጀመሩን፣ የክልሉ የፋይናንስ እና የሀብት ማስተባበሪያ ቢሮ ሓላፊ ዶክተር ምሕረት በየነ ገለጹ፡፡

የደመወዝ ክፍያው፣ የፌዴራሉ መንግሥት ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የላከውን በጀት መሠረት ያደረገ ሲኾን፣ ለመንግሥት ሠራተኞች የሦስት ወራት ደመወዛቸውን በመክፈል መጀመሩን፣ የቢሮ ሓላፊዋ ዶር. ምሕረት በየነ ገልጸዋል፡፡

በተያያዘ ዜና፣ ጦርነቱን ተከትሎ ከሥራ ቦታቸው ርቀው የቆዩ የመንግሥት ሠራተኞች፣ በተከታዮቹ ዐሥር ቀናት ውስጥ፣ ወደየመሥርያ ቤቶቻቸው ተመልሰው ሪፖርት እንዲያደርጉና መደበኛ ሥራቸውን እንዲጀምሩም፣ የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG