በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአጎዋ የእስከዛሬው ውጤት በመገምገም ላይ ነው


ፎቶ ፋይል፦ 18ኛው የአጎዋ ፎረም በአይቮሪኮስት
ፎቶ ፋይል፦ 18ኛው የአጎዋ ፎረም በአይቮሪኮስት

ከሰሃራ ግርጌ ላሉ አገሮች በአሜሪካ ሲተገበር የቆየው "አጎዋ" በመባል የሚታወቀው የተለየ የንግድ ፕሮግራም የአካባቢውን የጨርቃ ጨርቅ ዘርፍ በማሳደግ ረገድ ውጤታማ ቢሆንም፣ ጥቅሙ ግን በሁሉም አገሮች ያልተስፋፋ እና በሌሎች ዘርፎች ያልታየ መሆኑን ትናንት ለአሜሪካ ም/ቤት የቀረበ አንድ ሪፖርት ጠቁሟል።

የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት እንዳለው አጎዋ የተሰኘው ከቀረጥ ነጻ የንግድ ፕሮግራም በአንዳንድ አገሮች፣ በተለይም ለሴቶች ሥራን በመፍጠርና ድህነትን በመቀነስ ረገድ አስተዋጽኦ አድርጓል።

ከነዳጅ ውጪ ያሉና ሸቀጦች ከቀረጥ ነጻ በሚገቡበት ፕሮግራም እአአ ከ2014 እስከ 2021 ባሉት ሰባት ዓመታት ውስጥ ወደ አሜሪካ የገቡት ሸቀጦች የመጡት ከአምስት አገራት ብቻ መሆኑን ሪፖርቱ አመልክቷል። እነዚህም ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ሌሶቶ፣ ማዳጋስካር እና ኢትዮጵያ መሆናቸው ታውቋል።

በም/ቤቱ ጥያቄ መሠረት የተዘጋጀው ሪፖርት በመስከረም 2017 የሚያከትመውን የአጎዋ ፕሮግራም መቀጠል ወይም ማስተካከል ያስፈልግ እንደሁ በም/ቤቱ ለሚደረገው ክርክር ግበአት ይሆና ተብሏል።

በአሜሪካና አፍሪካ መካከል የንግድ መልህቅ ተደርጎ የሚቆጠረው አጎዋ ከሰሃራ በታች ያሉ አገራትን ምጣኔ ሃብትና ዲሞክራሲ ለማጎልበት በሚል በ1992 ዓ/ም የተጀመረ ሲሆን፣ በተጠቀሱት የአፍሪካ አገሮች በጨርቃጨርቅ ዘርፍ ስኬታማ ውጤት ያሳየ ሲሆን፣ ድህነትን በመስቀነስም ረገድ አስተዋጾኦ ማድረጉን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG