በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንድ የተከበሩ የሩሲያ የጦር ሹም ወደ ዩክሬን ተመለሱ


በዩክሬን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ከደረሰ የአየር ድብደባ የተረፉ ቅዱሳን ስዕሎችን የሚሰበስቡ ሴት አዛውንት
በዩክሬን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ከደረሰ የአየር ድብደባ የተረፉ ቅዱሳን ስዕሎችን የሚሰበስቡ ሴት አዛውንት

የዩክሬን ፕሬዘዳንት ቮልደሚየር ዘለንስኪ ትላንት ቅዳሜ ባደረጉት ዕለታዊ መግለጫቸው የዩክሬንን የሰላም ቀመር በተመለከተ ከፈረንሳዩ አቻቸው ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ዘለግ ያለ ውይይት ማድረጋቸውን አስታወቁ። ዘለንስኪ ውይይታቸውን “ፍጹም ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበ እና ጠለቅ ያለ” ሲሉ ገልጸውታል። ሁለቱ መሪዎች በመጪው በጋ ስለሚደረገው የሰሜን አትላንቲክ ጦር የመሪዎች ስብሰባ በተመለከተም ተወያይተዋል።

በሌላ በኩል የብሪታንያ መከላከያ ሚኒስቴር በእሁድ እለት ባወጣው የስለላ መረጃ፤ የሩሲያ የዩክሬን ወረራ አስመልክቶ በሩስያ የቪዲቭ የአየር ወለድ ጦር አዛዥ የሆኑት ጄኔራል ኮሎኔል ሚካሂል ቴፕሊንስኪ በጥር 2023 ከስራቸው ከተሰናበቱ በኋላ በዩክሬን ወገን በትልቅ ሚና የመመለሳቸው "ዕድል በጣም ከፍተኛ ነው" ብሏል።

ሚኒስቴሩ ቴፕሊንስኪን “በደረጃ እና በማዕረግ ሩሲያ ውስጥ በሰፊው ከሚከበሩት ጥቂት ከፍተኛ ጄኔራሎች መካከል አንዱ ሳይሆኑ አይቀርም” ሲል ገልጿል። አያይዞም “በስራቸው ላይ የቅርብ ጊዜ የታየው ውዝግብ በሩሲያ በዩክሬን ስላለው የሩሲያ ወታደራዊ አካሄድ በአጠቃላይ በጦር ውስጥ ባሉ አንጃዎች መካከል ከፍተኛ አለመግባባት መኖሩን ያሳያል” ብሏል።

በተያያዘ ሩሲያ በተሰኘችው የዩክሬን ከተማ በፈጸመችው የአየር ድብደባ 21 ሰዎች ሞተዋል። ዘለንስኪ ስሎቫኒክ እና ዶንባስን ለማዳን የሚደረገው ተልዕኮ እንደሚቀጥል በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

በአንጻሩ ዛሬ በተከበረው የትንሳኤ ክብረበዓል ላይ የሩሲያው ፕሬዘዳንት ብላድሚር ፑቲን ሞስኮ በሚገኘው አዳኙ ክርስቶስ በተሰኘው የሩሲያ ኦርቶዶክስ ካቴድራል የቅዳሴ ስነስርዓት ላይ ታድመዋል።

XS
SM
MD
LG