- ሐሰተኛ መረጃዎችንና የጥላቻ ንግግሮችን በመመከት እና በማጋለጥ ላይ ያተኮረ ነው
በኢትዮጵያ፣ የማኅበራዊ ገጸ ድር መድረኮችን በመጠቀም እየተስፋፋ የመጣው፣ የሐሰተኛ እና የጥላቻ መረጃ ሥርጭት፣ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ እና ለመመከት የተቀናጀ ጥረት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ።
በሦስት የአገር ውስጥ ቋንቋዎች፣ በማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛዎች በተሰራጩ መረጃዎች ላይ ጥናት ማድረጋቸውን የሚገልጹ ኹለት አገር በቀል ድርጅቶች፣ የሐሰተኛ እና የጥላቻ መረጃ ሥርጭቱ፣ ከፍተኛ ከመኾኑ የተነሣ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን በዳሰሳ ጥናታቸው ማረጋገጣቸውን ገልጸዋል፡፡ ጉዳቱን ለመመከት እንዲያግዝም፣ “ግራ ቀኝ” በተሰኘ መርሐ ግብር ውሱን ዘመቻ መጀመራቸውን አስታውቀዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት(USAID) ድጋፍ የሚደረግለት “ግራ ቀኝ” የተሰኘው መርሐ ግብር የሚያስተባብረው ይኸው ዘመቻ፣ ከፍተኛ የተከታይ ቁጥር ያላቸው የማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛ መድረኮች እየተሳተፉበት እንደሚገኙ በአገር በቀል ድርጅቶቹ የተገለጸ ሲኾን፣ ሰፊ የሕዝብ ተሳትፎን ሊጋብዝ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡
በዚኽ ዙሪያ የተሰናዳውን ሙሉ ዘገባ ለማድመጥ የተያያዘውን ፋይል ይጫኑ።