በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታይዋን የቻይናን ወታደራዊ ልምምድ በቅርበት እየተከታተለች መሆኗን ገለጸች


እሁድ ሚያዚያ 9ም 2023 የቻይናው ሲሲቲቪ ይፋ ያደረገው የቪዲዮ ምስል ይቻይና የባህር ኃይል መርከቦች በታይዋን ባህር ክልል አቅራቢያ ወታደራዊ ልምምድ ሲያደርጉ ያሳያል።
እሁድ ሚያዚያ 9ም 2023 የቻይናው ሲሲቲቪ ይፋ ያደረገው የቪዲዮ ምስል ይቻይና የባህር ኃይል መርከቦች በታይዋን ባህር ክልል አቅራቢያ ወታደራዊ ልምምድ ሲያደርጉ ያሳያል።

ታይዋን ቻይና ዛሬ ለሦስተኛ ተከታታይ ቀን ያካሄደችውን ወታደራዊ ልምምድ በቅርበት እየተከታተለች መሆኗን አስታወቀች፡

ታይዋን እንዳለችው ቻይና ባለፈው ቅዳሜ ለጀመረችው ወታደራዊ ልምምዷ ብዛት ያላቸው የጦር አውሮፕላኖች እና 11 የጦር መርከቦች ወደ ታይዋን አቅጣጫ ልካለች፡፡

የቻይና የጦር ኃይል ልምምድታይዋንን በማጠር እና በደሴቲቱ ያሉ ዋና ዋና ዒላማዎች ላይ የሚካሄዱ ጥቃቶች ላይ ያተኮረ ልምምድ መሆኑን የቻይና መንግሥት ቴሌቭዢን ዘግቧል፡፡

ዛሬ የጃፓን የመከላከያ ሚንስቴር በሰጠው መግለጫ የቻይና አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ትናንት ዕሁድ ኦኪናዋ ደሴት አቅራቢያ የአየር እንቅስቃሴ ማካሄዱን አመልክቷል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ ዩ ኤስ ኤስ ሚሊየስ የተባለው ሚሳይል አውዳሚ መርከቧ በደቡብ ቻይና ባህር በሚገኙት ስፕራትሊ ደሴቶች አቅራቢያ ማለፉን ዛሬ ሰኞ አስታውቃለች፡፡

የታይዋን ፕሬዚደንት ሳይ ኢንግ ዌን የቻይናን ወታደራዊ ልምምድ አውግዘው “ከቻይና በኩል አምባገነናዊ ተስፋፊነት አደጋ የተጋረጠባት ሀገራችን ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከሌሎችም ዲሞክራሲያዊ ሀገሮች ጋር መስራቷን ተቀጥላለች” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG