በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምስራቅ ኮንጎ 20 ሰዎች በእስላማዊ መንግሥት ተባባሪ ቡድን ታጣቂዎች ተገደሉ ተባለ


ቡኒያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ
ቡኒያ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ

ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ ምስራቃዊ ግዛት ውስጥ በደረሰ ጥቃት ሀያ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ፡፡ ምንጮች እንዳሉት ግድያውን የፈጸሙት ጂሃዳዊ ቡድን በሆነው የእስላማዊ መንግሥት ታጣቂዎች ናቸው፡፡

ምስራቅ ኮንጎ የሚገኝ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት መሪው ፓትሪክ ሙኮሄ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰጡት ቃል የተባበሩት ዲሞክራሲያዊ ኅይሎች የተባለው ቡድን ታጣቂዎች ዐርብ ከቀትር በኋላ በሰሜን ኪቪ ክፍለ ግዛት ኦይቻ ከተማ ጥቃት አድርሰው የገደሏቸውን ሀያ አንድ ወንዶች እና ሴቶች አስከሬኖች ቆጥሬአለሁ ያሉ ሲሆን በከተማ ሆስፒታል የአስከሬን ማሳረፊያ ሰራተኛ በበኩላቸው 19 አስከሬኖች ተቀብለናል ብለዋል፡፡

የክፍለ ግዛቷ ወታደራዊ አስተዳዳሪ ቻርልስ ኢሁታ ጥቃቱ መድረሱን አረጋግጠው ግድያውን የፈጸመው ኤ ዲ ኤፍ የተባለው ቡድን መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ይኸው ቡድን በአጎራባቿ ኢቱሪ ክፍለ ሀገር ከሰላሳ የሚበልጡ ሰዎችን መግደሉን ኮንጎ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የኮንጎ አረጋጊ ተልዕኮ ሐሙስ ዕለት አስታውቋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ የኤ ዲ ኤፍ መሪው ሴካ ሙሳ ባሉኩን የሚመለከት መረጃ ለሚሰጥ 5 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሸልም ባለፈው ወር ማስታወቋ ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG