በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከወህኒ ቤት ያመለጠው ደቡብ አፍሪካዊው ደፋሪ ታንዛኒያ ውስጥ ተያዘ


ፋይል - ታቦ ቤስተር ከግድያ ጋር በተያያዘ በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ከተማ፣ እ.አ.አ ግንቦት 3 ቀን 2012 ዓ.ም በዌስተርን ኬፕ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲቀርብ
ፋይል - ታቦ ቤስተር ከግድያ ጋር በተያያዘ በደቡብ አፍሪካ ኬፕ ታውን ከተማ፣ እ.አ.አ ግንቦት 3 ቀን 2012 ዓ.ም በዌስተርን ኬፕ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲቀርብ

“የፌስቡኩ ደፋሪ” በሚል ቅጽል ስም የሚጠራውን እና በግድያ ወንጀል ተፈርዶበት ወህኒ ቤት የነበረውን ደቡብ አፍሪካዊ ታቦ ቤስተርን መያዛቸውን የታንዛኒያ ባለስልጣናት አስታወቁ፡፡

ሴቶችን በማህበራዊ መገናኛው ላይ እያማለለ በማግኘቱ የፊስቡክ ደፋሪ የተባለው የሠላሳ አምስት ዓመቱ ቤስተር በዚህ መንገድ ካገኛቸው ሴቶች መካከል አንደኛዋን በመግደል ወንጀል የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት ወህኒ ቤት ታስሮ ነበር፡፡

ባለፈው ዓመት ወህኒ ቤቱ ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ ተቃጥሎ እንደሞተ ተነግሮ የነበረ ሲሆን በዚህ ዓመት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ እየታየ ነው የሚል ወሬ ይሰማ ጀመር፡፡

በእሳት አደጋው ተቃጥሎ የሞተው ሰው አስከሬን ሲመረመር የሌላ ሰው ሆኖ በመገኘቱ ታቦ ቤስተር ከወህኒ ቤቱ እንዳመለጠ ታወቀ፡፡ የወህኒ ቤቱ ባለስልጣናት እንዲያመልጥ ረድተውት ይሆናል የሚል ጥያቄ ማስነሳቱም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG