በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
“በሳህል አካባቢ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ሕጻናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ይገጥማቸዋል” - ዩኒሴፍ

“በሳህል አካባቢ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ሕጻናት የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ይገጥማቸዋል” - ዩኒሴፍ


እያሻቀበ ባለው የምግብ ዋጋ፣ ግጭት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ፣ በአፍሪካ ሳህል ቀጠና ውስጥ የሚገኙ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሕጻናት በዚህ ዓመት ከፍተኛ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ይገጥማቸዋል ሲል የሕጻናት አድን ድርጅቱ ዩኒሴፍ አስጠነቀቀ።

በምዕራብ አፍሪካ በሚገኙ ሦስት የሳህል አካባቢ አገሮች ውስጥ የሚኖሩና ከአምስት ዓመት ዕድሜ በታች ያሉ 970 ሺህ ሕጻናት ይጫጫሉ ሲል የመንግሥታቱ ድርጅት የሕጻናት መርጃ ወኪል የሆነው ዩኒሴፍ በመግለጫው አስታውቋል። አገሮቹም፤ ቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ እና ኒጄር መሆናቸው ታውቋል።

የተጠቀሱት አገሮች ድሃ ከመሆናቸው በተጨማሪ የባህር በር የሌላቸውና ጂሃዲስቶችን በመዋጋት ላይ ያሉ መሆናቸውን ዩኒሴፍ በመግለጫው ጠቁሟል።

በጣም ከሚጎዱት አገሮች ውስጥ አንዷ በሆነችው ኒጄር 430 ሺህ ሕጻናት የምግብ እጥረቱ ይገጥማቸዋል። በማሊ ደግሞ 367 ሺህ ሕጻናት ይጫጫሉ ተብሏል።

በዚህ ዓመት በሳህል በሚገኙና ሰባት በሚሆኑ አገሮች የሕጻናት መጫጫት እንደሚከሰት ያስታወቀው ዩኒሴፍ፣ መንግሥታት ለችግሩ ትኩረት እንዲሰጡ ማሳሳቡን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG