በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ዴሞክራሲያዊ ሽግግርን የማንበሩ ስምምነት ዳግም ተጓተተ


ካርቱም፣ ሱዳን
ካርቱም፣ ሱዳን

በሱዳን ጦር ኃይል እና ኢመደበኛ በኾነው ድጋፍ ሰጪ ታጣቂ መካከል ተጀምሮ የተስተጓጎለውን፣ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ወደነበረበት የመመለስ የስምምነት ፊርማ፣ በመሀከላቸው በተነሣ ጭቅጭቅ ምክንያት ዳግም መጓተቱ ተገለጸ፡፡

"የነፃነት እና የለውጥ ዐዋጅ" የተባለው፣ አፍቃሬ ዴሞክራሲ ስብስብ፣ ዛሬ ሊከናወን ታቅዶ የነበረው የስምምነቱ ፊርማ፣ በመሀከላቸው በተከሠተ ጭቅጭቅ ምክንያት መዘግየቱን ትላንት አስታውቋል፡፡

የጦር ሠራዊቱ እና የፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሰጪው ኃይል፣ በስምምነቱ ውስጥ በሚካተተው የወታደራዊ ዘርፍ ማሻሻያ ላይ፣ አሁንም ድርድር ላይ እንደኾኑ አመልክቷል፡፡ ኹለቱ ወገኖች፣ የፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ኃይሉ ታጣቂዎች፣ ከጦር ሠራዊቱ ጋር እንደምን እንደሚዋሐዱ በመደራደር ላይ እንደኾኑ አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG