በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስንጥቁ ሲሽር ያማረው የአዳጊዋ ዕጣ ፈንታ


ስንጥቁ ሲሽር ያማረው የአዳጊዋ ዕጣ ፈንታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:09 0:00

ስንጥቁ ሲሽር ያማረው የአዳጊዋ ዕጣ ፈንታ

- የገባሬ ሠናዩ የነፃ ቀዶ ሕክምና በረከት በባሕር ዳር

አቶ ነጋ ይርዳው፣ በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ጀግና ቀበሌ ዳንጎ ጎጥ ነዋሪ ሲኾኑ፣ የስምንት ልጆች አባት አርሶ አደር ናቸው።

የስምንት ዓመት ዓመት አዳጊ ሴት ልጃቸው የሠራሽ ያውቃል ነጋ፣ በተፈጥሮ የሚያጋጥም የከንፈር እና የላንቃ መሰንጠቅ የሚያስከትል የጤና እክል ተጋላጭ ነበረች።

በአንድ ገባሬ ሠናይ ድርጅት አማካይነት የሚሰጥ ነፃ የቀዶ ሕክምና ፍለጋ ላይ በነበሩበት፣ ባሕር ዳር ጥበበ ግዮን ልዩ ሆስፒታል ያገኘናቸው አቶ ነጋ፣ ልጃቸው የችግሩ ተጋላጭ በመኾኗ፣ ከእኵዮቿ ጋራ መጫወትም ኾነ መቀላቀል እንዳትችል እንዳደረጋት ይናገራሉ።

ነፃ የቀዶ ሕክምና

አገልግሎቱን የሚሰጠው፣ ዋና መቀመጫውን በዩናይትድ ስቴትሷ የሜኒሶታ ክፍለ ግዛት ያደረገው፣ በእንግሊዝኛው አጠራር፣ "Children‘s Surgery International” የተባለ ዓለም አቀፍ ገባሬ ሠናይ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ በሚሰጠው ነፃ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት፣ ተጠቃሚ የኾኑት አርሶ አደር ነጋ ይርዳው፣ ልጃቸው ከውልደቷ የገጠማትን ችግር፣ ከፈጣሪ ቁጣ ጋራ አያይዘውት እንደነበርና ማኅበረሰቡም እነርሱን እንደ ኀጢአተኛ ይቆጥራቸው እንደነበር ተናግረዋል።

በቀላል የሕክምና ርዳታ የሚድነው ይኸው እክል፣ እርሳቸውንም ኾነ ሕፃን ልጃቸውን፣ ለከባድ የሥነ ልቡና ጫና ዳርጓቸው ነበር። ገባሬ ሠናይ ድርጅቱ፣ የችግሩ ሰለባ የኾኑ ሕፃናትን ከመርዳት ባለፈ፣ በሀገር ውስጥ ለሚገኙ ባለሞያዎች፣ የዕውቀት እና የቴክኖሎጅ ሽግግር እያደረገም ይገኛል።

ከዚኽ በተጨማሪ፣ የቀዶ ሕክምና አገልግሎቱን በዘላቂነት፣ በሀገር ውስጥ ለመስጠት የሚችሉበትን ኹኔታ ለማመቻቸት፣ ጥረቱ ተወጥኗል።

ነፃ የቀዶ ሕክምናው የተደረገላት፣ የስምንት ዓመቷን አዳጊ የሠራሽ ያውቃል ነጋ እና በግብርና ሥራ የሚተዳደሩት ወላጆቿ፣ ረዥም ርቀት ተጉዘው ሕክምናው ከተሰጠበት የባሕር ዳር ከተማ ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ፣ የቀዶ ሕክምናው እስኪጠናቀቅ የነበረውን ሒደት በመከታተል የተሰናዳውን ዘገባ፣ ከተያያዘው የቪዲዮ ምስል መከታተል ትችላላችኹ።

XS
SM
MD
LG