በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪካ ተቃዋሚ ፓርቲ ዐዲስ መሪ መረጠ


የደቡብ አፍሪካ ተቃዋሚ ፓርቲ ዐዲስ መሪ መረጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:52 0:00

የደቡብ አፍሪካ ተቃዋሚ ፓርቲ ዐዲስ መሪ መረጠ

· “ደቡብ አፍሪካውያን አማራጭ መንግሥት እንድንኾን ይጠብቁናል” - ዐዲሱ መሪ ጆን ስቴንሁይሰን

የደቡብ አፍሪካው ተቃዋሚ “ዴሞክራሲያዊ ጥምረት” ፓርቲ፣ ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት እንዲያገለግሉት፣ ዐዲስ መሪውን ጆን ስቴንሁይሰንን መርጧቸዋል።

ተቃዋሚ ፓርቲው፣ ጆን ስቴንሁይሰንን መሪው አድርጎ የመረጣቸው፣ሚድራንድ በሚገኘው ጋላገር የመሰብሰቢያ ማዕከል በአካሔደው የ2023 ዓ.ም(እ.አ.አ) ጉባኤው ላይ ነው።

ጆን ስቴንሁይሰንም የፓርቲውን የመምራት ሓላፊነት ለመረከብ የኦሆታ ንግግር አሰምተዋል፡፡ “በዚኽ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ፣ ያደረጋችኹልኝን ጥሪ ለመቀበል፣ ዛሬ ከፊታችኹ ለመቆም በመቻሌ ክብር ተሰምቶኛል፤” ያሉት ጆን ስቴንሁይሰንን፣ “ለኹላችሁም ያለኝ መልስ 'አዎ' ነው። አዎ፤ ዴሞክራሲያዊ ጥምረት ፓርቲ፣ እ.አ.አ በ2024 ለሚደረገው ምርጫ፣ አገሪቱን መምራት እንዲችል ለማድረግ ከእያንዳንዳችኹ ጋራ እሠራለኹ፤” ብለዋል።

በዚኽ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ፣ ያደረጋችኹልኝን ጥሪ ለመቀበል፣ ዛሬ ከፊታችኹ ለመቆም በመቻሌ ክብር ተሰምቶኛል፤”

ተፎካካሪያቸውን ምፎ ፋላትሴን አሸንፈው የፓርቲው መሪ ኾነው የተመረጡት ስቴንሁይሰን፣ በባለቤታቸው እና በሴቶች ልጆቻቸው ታጅበው ነው የኦሆታ ንግግራቸውን ያሰሙት፡፡ ተመራጩ መሪ፣ እ.አ.አ. በ2024፣ በደቡብ አፍሪካ በሚካሔደው አጠቃላይ ምርጫ፣ ፓርቲያቸው ተወዳዳሪ ኾኖ መመረጥ እንዲችል የማብቃት ሓላፊነት ተጥሎባቸዋል። “አሁን ጉዳዩ የዴሞክራቶች ፖለቲካ ሳይኾን፣ የዴሞክራሲ እና የደቡብ አፍሪካ ህልውና ጉዳይ ነው፤” ብለዋል ስቴንሁይሰን።

አያይዘውም፣ “እንደ እውነቱ ከኾነ፣ ደቡብ አፍሪካውያን ከአኹን በኋላ፣ የዴሞክራሲያዊ ጥምረት ፓርቲን ከብዙዎች መካከል እንደ አንድ ፓርቲ አድርገው መመልከት ይቅርና፣ ተቃዋሚ ፓርቲ ብቻ ነው ብለው አይጠብቁም።

ደቡብ አፍሪካውያን፥ አኹን እንድንነሣና ለደቡብ አፍሪካ አማራጭ የመንግሥት መሪ ኾነን እንድንገኝ ይጠብቁናል፤” በማለት ፓርቲው የሚጠብቀውን ከፍተኛ ሓላፊነት አስገንዝበዋል፡፡

በጉባኤው የተሳተፉት የፓርቲው አባላት ደስታቸውን የገለጹላቸው ጆን ስቴንሁይሰን፣ ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የዴሞክራሲያዊ ጥምረት ፓርቲ መሪ ኾነው ያገለግላሉ።

የኤኤፍፒን ዘገባ ስመኝሽ የቆየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡

XS
SM
MD
LG