በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዐዲስ አበባ ዙሪያ ቤቶች ፈረሳ እና የነዋሪዎች ሮሮ


አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ እና ቤታቸው መፍረሱን ከተቃወሙ ስማቸውን መግለፅ ካልፈለጉ አንድ ግለሰብ የተገኘ።
አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ እና ቤታቸው መፍረሱን ከተቃወሙ ስማቸውን መግለፅ ካልፈለጉ አንድ ግለሰብ የተገኘ።

በዐዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር፣ ሕገ ወጥ የተባሉ ቤቶችን የማፍረስ እና ነዋሪዎችን የማስነሣት ተግባር ተባብሶ ቀጥሏል፤ ሲሉ ተጎጂዎች ገለጹ።
አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ እና ቤታቸው መፍረሱን የተቃወሙ ግለሰቦች፣ ከእነቤተ ሰዎቻቸው፣ መጠለያ በማጣት ለችግር መጋለጣቸውን ተናግረዋል፡፡
ተጎጂዎች ስለ አቀረቡት ቅሬታ፣ ከሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ተሾመ አዱኛ/ዶክተር/፣ ምላሽ ለመጠየቅ፣ የእጅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ብንደውልም ሊነሣልን አልቻለም፡፡
ይኹን እንጂ ከንቲባው፣ ከዚኽ ቀደም ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ምላሽ፣ ርምጃው የተወሰደው፣ ሕገ ወጥ ግንባታ በአከናወኑቱ ላይ ነው፤ ማለታቸው ይታወሳል፡፡
ርምጃው ዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶችን የጣሰ እንደኾነ በመተቸት ትላንት መግለጫ ያወጣው ኢሰመኮ፣ በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ በተፈጸመው ቤቶችን የማፍረስ እና በግዳጅ የማስነሣት ርምጃ የተጎዱ ሰዎች፣ በሕጋዊ መንገድ የመኖሪያ ቤት ሊያገኙ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
የኮሚሽኑ የማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሥራ ክፍል ዳይሬክተር ዶ/ር ብራይትማን ገብረ ሚካኤል፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ ርምጃው እየተወሰደ ያለው፣ ኢትዮጵያ የአጸደቀችውን ዓለም አቀፍ ሕግ በተፃረረ መልኩ መኾኑን ተናግረዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:11:52 0:00

XS
SM
MD
LG