በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ወታደሮችን ገጭቷል የተባለ ፍልስጤማዊ ገደለች

በጋዛ ከእስራኤል ጋር በሚያዋስነው ድንበር የእስራኤል ወታደራዊ ጥቃትን በመቃወም ጎማዎችን ያቃጠሉ ፍልስጤማውያን ብሔራዊ ባንዲራቸውን ሲያወለብሉ እ.ኤ.አ. ጥር 26 ቀን 2023.
በጋዛ ከእስራኤል ጋር በሚያዋስነው ድንበር የእስራኤል ወታደራዊ ጥቃትን በመቃወም ጎማዎችን ያቃጠሉ ፍልስጤማውያን ብሔራዊ ባንዲራቸውን ሲያወለብሉ እ.ኤ.አ. ጥር 26 ቀን 2023.

የእስራኤል የጸጥታ ኃይሎች፣ ትናንት ቅዳሜ ምሽት አንድ ላይ የነበሩ ሶስት እስራኤላውያን ወታደሮችን በመኪናው ገጭቷል የተባለ ተጠርጣሪ ፍልስጤማዊን ተኩሰው መግደላቸው ተነገረ፡፡

የእስራኤል መከላከያ ሶስቱም ወታደሮች ህክምናቸውን እየተከታተሉ መሆናቸውን ገልጾ አንደኛው ጽኑ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን ትናንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

እስራኤል እና ፍልስጤማዊያን በኃይል በተያዘው ዌስት ባንክ የሚያደርጉት ግጭት ካለፈው ዓመት ወዲህ እየተባባሰ መምጣቱ ተመልክቷል፡፡

በዚሁ ግጭት በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ ቢያንስ 86 ፍልስጤማውያን በእስራኤል ወታደሮች መገደላቸውን አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ፍልስጤማዊያኑ በእስራኤላውያን ላይ ባደረሱት ጥቃት 15 ሰዎች መሞታቸውንም ዘገባው አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG