በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍጋኒስታን 3 እንግሊዛዊያን በታሊባን ታገቱ 


Afghanistan
Afghanistan

ሶስት እንግሊዛዊያን አፍጋኒስታን ውስጥ በታሊባን መታገታቸውን እንግሊዝ ውስጥ የሚገኝ መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት ዘ ፕሪሲዲየም ኔትዎርክ፣ ትናንት ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

አፍጋኒስታን ውስጥ የታገቱት ሶስቱ ወንዶች እንዲለቀቁ ቤተሰቦቻቸውን በመርዳት በቆንስላዎች በኩል ግንኙነት እያደረገ መሆኑን የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ግን የታሰሩትን ዜጎች አስመልክቶ በሁለቱ አገር ባለስልጣናት በኩልም ምንም ትርጉም ያለው ግንኙነት አለመደረጉን አመልክቷል፡፡

ባለፈው ዓመታ ታሊባን አንድ የቴሌቪዥን ካሜራ ባለሙያ እና አራት የእንግሊዝ ዜጎችን 6 ወራት ይዞ ካቆያቸው በኋላ መልቀቁን የኤኤፍፒ ዘገባ አስታውሷል፡፡

ታሊባን ሰዎቹን በስለላ የጠረጠራቸው መሆኑን ቢገልጽም፣ የእንግሊዝ መንግሥት ግን ዜጎቹ ፣ አፍጋኒስታን ውስጥ የእንግሊዝ መንግሥት በሚሰራው ሥራ ምንም ድርሻ የሌላቸው፣ ወደ አፍጋኒስታን የሄዱትም የእንግሊዝ መንግሥት ያወጣውን ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት፣ በራሳቸው ተነሳሽነት መሆኑን ገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG