በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትራምፕ ማክሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል


ፋይል - ሪፐብሊካኑ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪ ዶናልድ ትራምፕ እ.አ.አ በታህሳስ 29፣ 2015 ዓ.ም አዮዋ ላይ የምርጫ ቅስቀሳ ባደረጉበት ወቅት ንግግር ሲያደርጉ
ፋይል - ሪፐብሊካኑ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪ ዶናልድ ትራምፕ እ.አ.አ በታህሳስ 29፣ 2015 ዓ.ም አዮዋ ላይ የምርጫ ቅስቀሳ ባደረጉበት ወቅት ንግግር ሲያደርጉ

የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞውፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የፊታችን ማክሰኞ፣ በይፋ ተይዘው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፤ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዋይት ኃውስ፣ ፕሬዚዳንትነት ሥልጣን ላይ ተቀምጦ የሚያውቅ ሰው ፣ የወንጀል ክሥ ሲመሠረትበት ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ታይቶ በማያውቅ ኹኔታ፣ ኒውዮርክ የሚገኘው የዳኞች ስብስብ፣ ትራምፕ እ.አ.አ በ2016 በነበራቸው የምርጫ ዘመጫ ወቅት፣ ከአንዲት የወሲብ ፊልሞች ተዋናይት ጋራ ነበራቸው የተባለው ግንኙነት ይፋ እንዳይወጣ ዝም ለማሰኘት ገንዘብ ከፍለዋል፤ በሚል ክሥ እንዲመሠረትባቸው፣ ኀሙስ ዕለት ድምፅ ሰጥቷል።

የማንሃታን ወረዳ ዐቃቤ ሕግ አልቪን ብራግ ቢሮ በአወጣው መግለጫ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ፣ ትራምፕ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ በአዘዘው መሠረት፣ የዐቃቤ ሕግ ቢሮ የትራምፕን ጠበቃ ማነጋገሩን ገልጿል።

ትራምፕ እጃቸውን ለመስጠት፣ ከሚኖሩበት የፍሎሪዳ ግዛት፣ ወደ ኒውዮርክ መጓዝ ይኖርባቸዋል። የቀድሞው ፕሬዝዳንት፣ ባለፈው ዐርብ ዕለት በላኩት የምርጫ ማስኬጃ ገንዘብ ማሰባሰቢያ ኢሜይል፣ “የሚመጣውን አልፈራም” ሲሉ ክሣቸውን ለመከላከል መዘጋጀታቸውን አሳይተዋል፡፡

ይኹን እንጂ፣ የግላቸው በኾነው ትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ፣ ክሣቸውን የሚመለከቱትን ዳኛ፣ “ይጠሉኛል” ያሉት ትራምፕ፣ ባለፈው ዓመት ተቋማቸው፣ በታክስ ማጭበርበር ክሥ በተመሠረተበት ወቅት፣ “ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ነው ያስተናገዱኝ” በማለት፣ በዳኛው የተሰማቸውን ስጋት አጠናክረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG