በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የይገባኛል ጥያቄ በሚነሣበት የሶማሊያ ግዛት ዐዲስ ጦርነት ተቀሰቀሰ


የሶማሌላንድ ካርታ
የሶማሌላንድ ካርታ

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት፣ የሶማሌላንድ ወታደሮች ሶማሊያ ውስጥ ከሚገኘው ላሳኖድ ከተማ ለቀው እንዲወጡ ከጠየቀ ከኹለት ቀን በኋላ ቅዳሜ ጠዋት፣ ዐዲስ ውጊያ ተቀስቅሷል።

ላለፉት 50 ቀናት፣ የሶማሌላንድ ኃይሎች ከአካባቢው የሶማሊያ ሚሊሺያ ጋራ በአደረጉት ውጊያ፣ ከ200 በላይ ሰዎች ሲገደሉ፣ ከ600 በላይ የሚኾኑ ቆስለዋል።

በላሳኖድ የሚኖሩ ጎሣዎች፣ በሞቃዲሾ የፌዴራል መንግሥት ሥር ለመተዳደር ቢጠይቁም፣ የሶማሌላንድ ግዛት ግን፣ ግዛቱ በእርሷ ቁጥጥር ሥር እንደኾነ አሳውቃለች።

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት፣ ኀሙስ ዕለት፣ ሶማሌላንድ ኃይሏን ከከተማው እንድታስወጣና ግጭቱን በንግግር ለመፍታት መንገድ እንድትከፍት ጠይቃ ነበር፡፡ ሶማሌላንድ በበኩሏ፣ የአሜሪካ መንግሥት፣ ወደ ላሳኖድ ከተማ የሚጎርፉትን ተዋጊዎች እንዲያስቆም በፑንትላንድ መንግሥት ላይ ግፊት አላደረገም፤ ስትል ወቅሳለች።

ባለፈው ዐርብ፣ የሶማሌላንድ ኃይሎች፣ በከተማዪቱ ላይ በፈጸሙት የአየር ድብደባ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው፣ የሶማሌላንድ ጦር ላሳኖድ ከተማን ለመቆጣጠር ጥቃት እንደሚሰነዝር፣ ሰኞ ዕለት መግለጫ ከአወጣ በኋላ መኾኑ ተመልክቷል።

XS
SM
MD
LG