በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካማላ ሃሪስ በዛምቢያ ጉዞ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን አጠናቀቁ


በስተግራ የሚታዩት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ በሉሳካ፣ ዛምቢያ ሲደርሱ ባህላዊ ተውዛዋዦች አቀባበል አድርገውላቸዋል
በስተግራ የሚታዩት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ በሉሳካ፣ ዛምቢያ ሲደርሱ ባህላዊ ተውዛዋዦች አቀባበል አድርገውላቸዋል

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ፣ በአፍሪካ ያደረጉትን የአንድ ሳምንት ጉብኝት ለማጠቃለል ዛምቢያ የገቡት ትላንት ነበር። በዛምቢያ በነበራቸው ቆይታም፣ በዕዳ ማስተካከል ዙሪያ፣ ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ጋራ የተወያዩ ሲኾን፣ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ ለመላመድ እና ጉዳቱን ለመግታት የሚውል፣ ከሰባት ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ ድጋፍ፣ ለግሉ ዘርፍ እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል።

ካማላ ሃሪስ በዛምቢያ ቆይታቸው፣ አያታቸው ይኖሩበት የነበረውንና በልጅነታቸው የጎበኙትን በማዕከላዊ ሉሳካ የሚገኝ ስፍራም ጎብኝተዋል።

ወደብ አልባ የኾነችው ዛምቢያ፣ በመዳብ ማዕድን የበለጸገች ብትኾንም፣ እ.አ.አ. በ2010 የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ሲነሣ፣ አገሪቱ ያለባትን ዕዳም ኾነ ወለዱን መክፈል ያልቻለች፣ የመጀመሪያዪቱ አፍሪካዊት ሀገር ናት።

ዐርብ ዕለት ከሃሪስ ጋራ የተገናኙት የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሀካንዴ ሂቺሌማ፣ ዩናይትድ ስቴትስ አገሪቱ ያለባትን የ15 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ በመሰረዝ፣ ወለዱን በመቀነስ እና የክፍያ ጊዜውን በማራዘም በመሰሉት የድጋፍ አማራጮች እንድትረዳ ጠይቀዋል።

ሃሪስ በበኩላቸው፣ የፀረ ሙስና ጥረቶችን፣ ኢኮኖሚያዊ እና ዴሞክራሲያዊ ማሻሻያዎችን፣ ግብርናንና ሌሎችንም ዘርፎች የሚሸፍን ድጋፍ፣ ለግሉ እና የመንግሥት ዘርፎች ለማድረግ ቃል ገብተው፣ በአብዛኛው፣ ከቻይና የተገኘውን ብድርም ለማስተካከል የቀረበውን ጥሪ እንደሚደግፉ ገልጸዋል።

ካማላ ሃሪስ የአፍሪካ ጉዟቸውን አጠናቅቀው፣ ነገ እሑድ ወደ ዋሽንግተን እንደሚመለሱ ተጠቁሟል።

XS
SM
MD
LG