በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የፒያኖዋ እመቤት" እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ ቀብር አርብ በእስራኤል ይፈጸማል


"የፒያኖዋ እመቤት" እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ ቀብር አርብ በእስራኤል ይፈጸማል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:06 0:00

"የፒያኖዋ እመቤት" እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ ቀብር እሑድ በእስራኤል ይፈጸማል

►ታሪካዊ ፒያኖአቸውን ለያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ተናዘዋል

ለኢትዮጵያ የረቂቅ ሙዚቃ ዘርፍ በአበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ የሚታወቁት፣ የእማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ የቀብር ሥነ ሥርዐት፣ በመጪው አርብ፣ በእስራኤል ኢየሩሳሌም ከተማ እንደሚፈጸም ቤተ ሰዎቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።

የ"ፒያኖዋ እመቤት" በመባል የሚታወቁት እና ከ300 በላይ ረቂቅ ሙዚቃዎችን ለአድማጭ ያቀረቡት እማሆይ ጽጌ ማርያም፣ ለዓመታት የተጠቀሙበት ታሪካዊ ፒያኖ፣ ለያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት እንዲሰጥ መናዘዛቸውን፣ በስማቸው የተሰየመው ፋውንዴሽን መሥራችና የእህታቸው ልጅ ሐና ከበደ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ለዓመታት የተጠቀሙበት ታሪካዊ ፒያኖ፣ ለያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት እንዲሰጥ መናዘዛቸውን፣ በስማቸው የተሰየመው ፋውንዴሽን መሥራችና የእህታቸው ልጅ ሐና ከበደ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በ99 ዓመት ዕድሜአቸው ከዚኽ ዓለም በሞት ስለተለዩት እማሆይ ጽጌ ማርያም፣ ኅልፈተ ሕይወት የጠየቅናቸው ሥርዓተ ቀብራቸውን ለማስፈጸም ወደ እስራኤል ከአቀኑት የእማሆይ የሥጋ ዘመዶች መካከል አንዷ የኾኑት ሐና ከበደ ሃኪም ቤት ውስጥ እያሉ ከዚኽ ዓለም በሞት መለየታቸውን ገልፀውልናል።

በ1916 ዓ.ም ከአባታቸው ከንቲባ ገብሩ ደስታ ከእናታቸው ወ/ሮ ካሳዬ የለምቱ በዐዲስ አበባ ከተማ የተወለዱት እማሆይ ጽጌ ማርያም፣ ከምንኵስና በፊት የተጽውኦ ስማቸው የውብዳር ገብሩ ነበር።

በስድስት ዓመታቸው ወደ ስዊዘርላንድ ተልከው፣ ፒያኖ እና ቫዮሊን ያጠኑት እማሆይ፣ በ14 ዓመታቸው ከእነቤተሰባቸው ታስረው ወደ ጣልያን ተወስደዋል። ጣልያን ድል ከኾነ በኋላ ወደ ሀገራቸው በመመለስ በተለያዩ ኪነ ጥበብ ተኮር ሓላፊነቶች አገልግለዋል። በ21 ዓመታቸው ከዓለማዊው አኗኗር በመለየት ከመነኑ በኋላ ተሰጥኦዋቸውን፣ ለበርካቶች የጥልቅ ጥሞና እና የደግነት ምንጭ ይኾን ዘንድ አውለውታል።

ከሥራዎቻቸው የሚገኝ ገቢን፣ ወላጆቻቸውን ለዐጡ ሕፃናት ማሳደጊያ፣ ለአብነት/የቆሎ/ ተማሪዎች እገዛ እንዲውል ማድረግን በመሳሰሉ ግብረ ሠናይ እንቅስቃሴዎች የሚታወቁት እማሆይ፣ ከ1977 ዓ.ም. ጀምሮ ነዋሪነታቸውን በሀገረ እስራኤል ኢየሩሳሌም አድርገው ነበር።

"የፒያኖዋ እመቤት" እማሆይ ጽጌ ማርያም ገብሩ፣ በአሳለፍነው እሑድ በ99 ዓመታቸው ከዚኽ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሥርዓተ ቀብራቸውም፣ ለ40 ዓመት ያህል መንፈሳዊ አገልግሎት በሰጡበት በኢየሩሳሌም ከተማ እንደሚፈጸም፤ ሥራቸው እና ታሪካቸው ተጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ የሚሠራው በስማቸው የተቋቋመው ፋውንዴሽን አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG