በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በመቆሙ አዲስ ሥምምነት ለማድረግ ተስፋ አለ - አይኤምኤፍ


የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በመቆሙ በአዲስ መልክ ከኢትዮጵያ ጋር ለመሥራት ተስፋ እንደሰጠና በኢትዮጵያ በኩል የቀረበውን የገንዘብ ዕርዳታ በተመለከተ ቴክኒካዊ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ትናንት አስታውቋል።

የተቋሙ ቃል አቀባይ ጁሊ ኮዛክ ዋሽንግተን ላይ ለዜና ሰዎች እንደተናገሩት፣ የበርካታ አፍሪካ አገራትን ኢኮኖሚና የፋይናንስ ሁኔታ ለማረጋጋት አብሮ እየሰራ መሆኑንና ኢትዮጵያን በተመለከተም ተቋሙ የተደረሰውን የሰላም ሥምምነት በበጎ እንደተቀበለ፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር የኢኮኖሚ ተሃድሶ ዕቅድን በተመለከተ ውይይት በመደረግ ላይ መሆኑ ታውቋል።

ቃል አቀባይዋ በመቀጠል እንዳሉት ተቋሙ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚም ሆነ የሰብዓዊ ተግዳሮቶችን በተመለከተ እንዴት መርዳት እንደሚችል ከባለሥልጣናት ጋር በመምከር ላይ ነው።

የሰላም ሥምምነቱ ትግበራ በጥሩ እየሄደ መሆኑንና የሰብዓዊ ዕርዳታና መሠረታዊ አገልግሎቶች በትግራይ ክልል መመለሳቸው በመልካም የሚታይ መሆኑን ቃል አቀባይዋ ጭምረው ተናግረዋል።

በተመሳሳይ አይኤምኤፍ ከጋና እና ዛምብያ ጋርም በተለያዩ መስኮች አብሮ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG