በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በድርቅ የተጎዱ የደራሼ፣ የቡርጂና አማሮ አርሶ አደሮች እርዳታ እየጠየቁ ነው


በድርቅ የተጎዱ የደራሼ፣ የቡርጂና አማሮ አርሶ አደሮች እርዳታ እየጠየቁ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:49 0:00

በድርቅ የተጎዱ የደራሼ፣ የቡርጂና አማሮ አርሶ አደሮች እርዳታ እየጠየቁ ነው

በተደጋጋሚ የእርዳታ ጥሪ ቢያሰሙም ሰብዓዊ ድጋፍ ያለማግኘታቸውን በደቡብ ክልል በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የተጋለጡ የየአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ተናገሩ።

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የደራሼ፣ የቡርጂ እና አማሮ ልዩ ወረዳዎች አርሶ አደሮች በአካባቢዎቹ በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ገልጸው፤ ዝናብ መጣል ቢጅምር እንኳን ለዘር የሚውል አዝርት ጭምር እንደሌላቸው አመልክተዋል።

የደቡብ ክልል መንግሥት በበኩሉ በድርቅ ለተጎዱ አርሶ አደሮች በ100 ሚሊዮን የገዛውን እህል እያጓጓዘ መሆኑን የክልሉ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል።

በ40 ሚሊየን ብር ወጪ ምርጥ ዘር ገዝቶ እያቀረበ ስለመሆኑም የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰሎሞን ትናንት በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል።

በፌዴራል መንግሥት እንዲደገፉ በመወሰኑ ይኼኛው ድጋፍ በደቡብ ኦሞ እና ኮንሶ ዞን ለድርቅ የተጋለጡትን አያካትትም ተብሏል።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG