በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካዊው የረድኤት ሠራተኛና ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ ከእገታ ተለቀቁ


አሜሪካዊው የረድኤት ሠራተኛና ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ ከእገታ ተለቀቁ
አሜሪካዊው የረድኤት ሠራተኛና ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ ከእገታ ተለቀቁ

ከስድስት ዓመታት በፊት በእአአ 2016 ኒጀር ውስጥ ተጠልፎ የነበረው አሜሪካዊው የረድኤት ሠራተኛ ጀፈሪ ዉድኪ እና ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ ኦሊቪዬ ዱቧ ከታገቱበት ተለቀው ኒያሚ አውሮፕላን ጣቢያ መድረሳቸውን መመልከቱን የኤኤፍፒ ጋዜጠኛ በሪፖርቱ አመልክቷል።

ከስድስት ዓመታት በፊት ጠባቂውን ከገደሉ በኋላ የረዴት ሠራተኛውን ታጣቂዎች ወደ ማሊ ጠረፍ እንደወሰዱት ሲገመት፣ ስለተለቀቀበት መንገድ ብዙም መረጃ አልተገኘም።

አሜሪካ ለኒጄር ምስጋና እንዳቀረበች ለማወቅ ተችሏል።

ከሁለት ዓመታት በፊት ሳህል ውስጥ በጂሃዲስቶች ተጠልፎ የነበረው የፈረንሳዊው ጋዜጠኛ ኦሊቪዬ ዱቧም በተመሳሳይ መለቀቁ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG