በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢኳዶርና ፔሩ በተከሰተ የመሬት መራድ 15 ሞቱ


እ.አ.አ 2016 በኢኳዶር የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ (ፎቶ ፋይል አሶስዬትድ ፕረስ)
እ.አ.አ 2016 በኢኳዶር የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ (ፎቶ ፋይል አሶስዬትድ ፕረስ)

6.8 ሬክተር ስኬል ያለው የመሬት መንቀጥቅጥ ኢኳዶርንና በከፊል ፔሩን ሲመታ 15 የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በመቶ የሚቆጠሩ ደግም መጎዳታቸው ታውቋል።

አብዛኛው ሞት የተከሰተው በኢኳዶር መሆኑም ታውቋል።

የኢኳዶሩ ፕሬዝደንት ጊሊርሞ ላሶ በትዊተር እንዳስታወቁት፣ የአደጋ ግዜ ሰራተኞች የተጎዱትን ለመርዳት ተሰማርተዋል።

የአሜሪካ የአየር ንብረት አገልግሎት የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሉ ሱናሚ ይከተል እንደሁ ማስጠንቀቂያ አልሰጠም።

አብዛኞቹ የፈረሱት ቤቶች የሚያመሳስላቸው አሮጌና በብዛት ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሰዎች መኖሪያ መሆናቸው መሆኑን አሶስዪትድ ፕረስ በዘገባው አመልክቷል። የመሬት መራድን የሚከላከል አሰራር እንዳልተከተሉም ሪፖርቱ ጠቁሟል።

XS
SM
MD
LG