በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በታንዛኒያ ምንነቱ ያልታወቀ ህመም አምስት ሰዎችን ገደለ


የታንዛኒያ ካርታ
የታንዛኒያ ካርታ

የታንዛኒያ ባለስልጣናት በሀገሪቱ ሰሜናዊ ምዕራብ ኢቦላ በሚመስሉ ምልክቶች አምስት ሰዎችን የገደለውን ህመም እያጣሩ ሲሆን፣ ገዳይ ቫይረስ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል።

የታንዛኒያ የጤና ሚኒስትር ሐሙስ ምሽት ባወጣው መግለጫ በሰሜን ምዕራብ ካጄራ ክልል በበሽታው የተያዙት ሰባት ሰዎች እንደ ትኩሳት፣ ማስታወክ፣ የደም መፍሰስ እና የኩላሊት ስራ ማቆም የመሳሰሉ ምልክቶች ታይተውባቸዋል ብሏል።

በክልል እና በምክር ቤት ደረጃ ያሉ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ሰጪ ቡድኖች ምንነቱ ያልታወቀውን በሽታ ለመመርመር እና ለመረዳት ወደ ቦታው መንቀሳቀሳቸውን ዋና የህክምና መኮንን ቱማኢኒ ናጉ ገልፀዋል።

የበሽታዎቹ ምልክቶች የሆኑት ሀይለኛ ትኩሳት፣ ከፍተኛ ደም መፍሰስ እና የሰውነት አካል ክፍሎች ስራ ማቆም ገዳይ ከሆነው የኢቦላ በሽታ ምልክቶች ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ተገልጿል።

በሽታው የተገኘበት ካጌራ ክልል በዩጋንዳ ድምበር ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በዩጋንዳ ከመስከረም እስከ ጥር ድረስ በተከሰተ የሱዳን ዝርያ ያለው የኢቦላ በሽታ ምክንያት የ77 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG