በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከጃፓን የተመለሱት የደ.ኮሪያ ፕሬዚዳንት ተቃውሞ ገጠማቸው


ከጃፓን የተመለሱት የደ.ኮሪያ ፕሬዚዳንት ተቃውሞ ገጠማቸው
ከጃፓን የተመለሱት የደ.ኮሪያ ፕሬዚዳንት ተቃውሞ ገጠማቸው

የደቡብ ኮሪያና የጃፓንን አዲስ ግንኙነት በማደስ አዲስ ምዕራፍ ለመክፍት ታቅዶ ከተካሄደው ጉባኤ የተመለሱት የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ዩን ሴኦክ ዬኦል ከአገሪቱ የግራ ዘመም ተቃዋሚ ፓርቲ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው፡፡

በ12 ዓመት ታሪክ ውስጥ በቶኪዮ ከጃፓኑ አቻቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሻዳ ጋር የሁለትዮሽ ስብሰባ ሲያደርጉ፣ ዩን የመጀመሪያው የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ሁለቱ መሪዎች በየጊዜው አንዳቸው የሌላኛውን አገር በመደበኝነት እንዲጎበኙ ሲስማሙ፣ የንግድ ግንኙነታቸውን ለማጠንከር፣ ከቻይናና ሰሜን ኮሪያ ከመሳሰሉ አገሮች የተደቀኑትን የጋራ አደጋዎች ለመመከት የደህንነት ትብብር ለማድረግ መስማማታችው ተገልጿል፡፡

የስብሰባው ውጤት ከፍተኛ ተቃውሞ የቀሰቀሱትን ግራ ዘመሞቹን የደቡብ ኮሪያ ፖለቲከኞች አላረካም፡፡

ተቃዋሚዎቹ ዩንን የሚተቹት ከጃፓን ጋር ለረጅም ጊዜ የቆየውን ታሪካዊ ቁርሾና አለመግባባት በማንሳት ነው፡፡

“የትናንቱ የደቡብ ኮሪያ ጃፓን ጉባኤ እጅግ አሳፋሪና በደቡብ ኮሪያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ጥፋት የታየበት ነው፡፡” ሲሉ የተቃዋሚው የዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪ ሊ ጄ ሙያንግ ተናግረዋል፡፡

“ለጃፓን ግብር የምንከፍል፣ እርቅን የምንለምንና እጅ የሰጠን ያስመስለናል” በማለት፣ ሊ በፓርቲው ስብሰባ ላይ መናገራቸው ተገልጿል፡፡

ጃፓን የደቡብ ኮሪያን ሴቶች ለአስገዳጅ የወሲብ ባርነት መዳረግን ጨምሮ፣ በጦርነቱ ወቅት የደቡብ ኮሪያን ጉልበት በዝብዛለች በሚል፣ ካሳ መክፈል እና ይቅርታ መጠየቅ ይገባታል የሚል ጥያቄ በተራማጁ የደቡብ ኮሪያ ወገን በኩል በየጊዜው የሚነሳ ጥያቄ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG