የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ትናንት ሀሙስ ለአፍሪካ የሳህል ክልል አዲስ የ150 ሚሊዮን ዶላር ሰብአዊ እርዳታ ይፋ አድርገዋል።
እርዳታው በግጭትና በምግብ ዋስትና ደህንነት ለተጎዱ ስደተኞች የነፍስ አድን ድጋፍ እንደሚውልም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ብሊንከን እርዳታውን ይፋ ያደረጉት ኒጀርን በጎበኙበት ወቅት ሲሆን የገንዘብ ድጋፉ ለቡርኪናፋሶ፣ ቻድ፣ ማሊ እና ሞሪታኒያ ጭምር እንደሚውል ገልፀዋል።
ጥቅል እርዳታው ሊቢያ እና ኒጀር ውስጥ የሚገኙ የሳህል ስደተኞችንም ይጨምራል ብለዋል ብሊንከን።