በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስና ሩሲያ በምዕራብ አፍሪካ ለተጽዕኖ እየተፎካከሩ ነው


በጋና የጸረ ሽብር ዘመቻ ወታደራዊ ልምድድ፣ ዳቦያ፣ ጋና
በጋና የጸረ ሽብር ዘመቻ ወታደራዊ ልምድድ፣ ዳቦያ፣ ጋና

ከሩሲያው የዩክሬን ወረራ በኋላ ግንኙነታቸው የበለጠ እየሻከረ የመጣው ዩናትይድ ስቴትስና ሩሲያ በምዕራብ አፍሪካ የበላይነትን ለመቆጣጠር እየተፎካከሩ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በጋና የጸረ ሽብር ዘመቻው ወታደራዊ ልምድድ በዩናይትድ ስቴትስ የጦር አዛዦች መሪነት እየተካሄደ ሲሆን፣ ሩሲያም እንደ ማሊ ባሉ አገሮች ወታደራዊ ሥልጠናዎችን እየሰጠች መሆኑን ተዘግቧል፡፡

የዩናይትድ ስቴትሱ ኮሎኔል ሮበርት ዚላ በባህር ዳርቻው የሚገኙ የምዕራብ አፍሪካ አገሮች ምዕራባውያን ባልሆኑ እንደ ሩሲያ ባሉ ኃይሎች ከመተማመን ይልቅ፣ አገሮቹ እርስ በእርሳቸው አጠገባቸው ካሉ ጎረቤት አገሮች ጋር ተባብረው የጋራ ችግሮቻቸውን ለማስወገድ እንዲሰሩ ይመክራሉ፡፡ የእንደዚህ ዓይነቶቹ ፖሊሲዎች መቀጠል ዩናይትድ ስቴትስንም እንደሚጠቅሙ ኮሌኒሉ ይናገራሉ፡፡

በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን የጨበጡት የማሊ ወታደራዊ መሪዎች ሽብርተኞችን ለመቋቋም በግል የሚንቀሳቀሰው የሩሲያውን ቅጥረኛውን ዋግነር ቡድን ጦር አስገብተዋል፡፡

ምዕራባዊያን መንግሥታት እና የተባበሩት መንግሥታት ግን እስላማዊ ቡድን ሽብርተኞቹ አለመጥፋታቸውንና ይልቁንም የሚያደርሱት ጥፋት እየጨመረ መምጣቱን ይናገራሉ፡፡

የማሊ ወታደራው ገዥዎች ግን የሩሲያ ኃይሎች ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ሳይሆኑ የአገር ውስጥ ወታደሮችን ስለሩሲያ መሳሪያዎች ሥልጠና በመስጠት የሚረዱ ናቸው ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

እስላማዊ አማጽያንን ለማስቆም የሚደረገው ጥረት ባለመሳካቱ፣ ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ሲጠፋ በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ደግሞ እንዲፈናቀሉ ማድረጉ ተመልክቷል፡፡

በሺዎቹ የሚቆጠሩ የፈረንሳይ ወታደሮች ከማሊና ቡርኪናፋሶና በወታደራዊ ጁንታዎች እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ሁኔታዎች እየተባባሱ መምጣቱን የደህንነት ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለም ዩናይትድ ስቴትስ ከጦር ሜዳ ውጭ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደገና ለመፍጠር እየሞከረች ነው፡፡

በዚህ ሳምንት የዩናይትድ ስትቴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር በመገናኘት፣ ሁለቱም አገሮች አገር ውስጥ በነበረው ጦርነት ተጎድቶ የነበረውን የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ለማደስ ጥረት ማድረጋቸው ተመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ ዩናይትድ ስቴትስ ለአፍሪካ መስጠት የምትፈልገው እርዳታ ምን ሊሆን እንደሚችል ግልጽ አለመሆኑ ዘገባው አመልክቷል፡፡

በኒዥርም እኤአ በ2017 አራት ወታደሮች ከተገደሉ በኋላ ያለውን ግንኙነት እንደገና ለማጠናከር ማቅማማት መኖሩ የተነገረ ሲሆን፣ የእስልምና አክራሪዎች እየተስፋፉ ከመጡ በኋላ ግን ያለው ጊዜ አጭር መሆኑን ተችዎች ተናረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG