በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ 331 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገባች


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ኢትዮጵያ ለሚያስፈልጋት የሰብዓዊ ዕርዳታ የሚውል 331 ሚሊየን ዶላር እንደምትሰጥ ዛሬ አስታወቁ።

የገንዘብ ድጋፉ በኢትዮጵያ በግጭት፣ በድርቅ እና በምግብ ዕጦት ለተፈናቀሉ እና ለተጎዱ ዜጎች ህይወት አድን ድጋፍ ለማድረግ እንደሚውልም ገልፀዋል።

ከተጠቀሰው ገንዘብ 12 ሚሊየን ዶላር የሚሆነው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሕዝብ፣ የስደተኞች እና የፍልሰት ቢሮ በኩል የሚሰጥ ሲሆን ከ319 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚሆነው ደግሞ በዩናይት ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ (USAID) በኩል የሚሰጥ ይሆናል።

ይህም አሜሪካ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2023 በቀጠናው ለሰብዓዊ እርዳታ እንዲውል የምትሰጠውን እርዳታ ወደ 780 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ከፍ እንደሚያደርገው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁን የሰብአዊ እርዳታ አቅራቢ ሀገር መሆኗን ያመለከተው መግለጫ፣ አዲስ ይፋ የተደረገው የዕርዳታ ገንዘብ በዩናይትድ ስቴትስ እና በአፍሪካ መካከል ያለውን አጋርነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ጨምሮ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG