በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኒጀር 30 ጂሃዲስቶችን ገድያለሁ አለች


በጅሃዲስቶች ጥቃት ስር ያለችው ኒጀር ባለፈው ሳምንት 30 የቦኮ ሃራም ታጣቂ ቡድን አባላትን መግደሏን አስታወቀች፡፡

960 የሚደርሱ አብዛኞቹ ሴቶችና ህጻናት ያሉበት የቡድኑ ተከታዮችም ወደ አጎራባች አገር ናይጄሪያ መሰደዳቸውን የባለሥልጣናትን ምንጮች የጠቀሰው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት ሴቶችና ህጻናት፣ ዲፋ ወደ ተባለው ከተማ መወሰዳቸውን የናይጄሪያ ጦር ባለሥልጣናት ገልጸዋል፡፡

የሳቢሚሳ አካባቢን በመልቀቅ የተሰደዱt በርካታ ቁጥር ያላቸው የቦካሃራም ታጣቂዎች በኒጀርና ናይጄሪያ ድንበር ላይ መያዛቸውን ባለሥልጣናቱ ገልጸዋል፡፡ እኤአ ከ2009 ጁምሮ ቦኮ ሃራም ባደረሰው ጥቃት ከ40ሺ በላይ ሰዎችን ሲገድል ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉትን ደግሞ እንዲፈናቀሉ ማድረጉን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የዩናይት ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከዛሬው የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው በኋላ ወደ ኒጀር እንደሚያመሩ ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG