በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይናው ሺ ከሳዑዲ እና ኢራን ሥምምነት በኋላ በዓለም ትልቁን ድርሻ ይፈልጋሉ


የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ
የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ ቤጂንግ ሳኡዲ አረብያ እና ኢራን የተቋረጠ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ለመቀጠል የተስማሙበትን ንግግር በማስተናገድ የዲፕሎማቲክ ድል ከተቀዳጀች በኋላ ቻይና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ትልቅ ሚና እንድትጫወት ጥሪ አድርገዋል፡፡

ሺ ይህን የተናገሩት ኢኮኖሚውንና ማኅበረሰቡን ለመቆጣጠር የሚያስችላቸውን የታማኞች መንግሥት የመሰረቱበትን የህግ አውጭዎች ስብሰባ ካካሄዱ በኋላ መሆኑን የአሶሴይትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ቻይና “የዓለም አቀፉን አስተዳደር ሥርዓት ተሀድሶም ሆነ ግንባታ ላይ በንቃት መሳተፍ ይኖርባታል” እንዲሁም “የዓለም ደህንነት ተነሳሽነትን” ማስተዋወቅ አለባት” ሲሉም በአስርት ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያላቸው ሺ፣ ለወጉ በተደረገው የህግ አውጭዎች ስብሰባ ማጠናቀቂያ ላይ ተናግረዋል፡፡

ሺ አክለውም “ ያ በዓለም አቀፉ ሰላም ላይ አሉታዊና አበረታች ኃይል የሚሰጥና በጎ ድባብ የሚፈጥር ሲሆን ለአገራችን ልማትም ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል፡፡

ሺ የገዥው ኮሚኒስት ፓርቲን ትልሞች ዝርዝር ባይገልጹም እኤአ በ2012 እሳቸው ሥልጣኑን ከያዙ ወዲህ መንግሥታቸው ጠንከር ያሉ ፖሊሲዎችን ማውጣት መጀመሩ ተመልክቷል፡፡

ቤጂንግ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድና ሌሎች ተቋማት የታዳጊ አገሮችን ፍላጎት ማሟላት አልቻሉም ትላለች፡፡

XS
SM
MD
LG