በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እየጠነከረ ያለው ድርቅ ሴቶችን በበለጠ እየጎዳ ነው


እየጠነከረ ያለው ድርቅ ሴቶችን በበለጠ እየጎዳ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:02 0:00

እየጠነከረ ያለው ድርቅ ሴቶችን በበለጠ እየጎዳ ነው

ከፍተኛ ተለዋዋጭ የአየር ሁኔታ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ለውጡ የሚያስከትላቸው እንደ ድርቅ የመሳሰሉ አደጋዎች ባልተመጣጠነ ሁኔታ ሴቶች ላይ ተፅእኖ እንደሚያደርሱ በርካታ ጥናቶች ያሳያሉ። በ60 ዓመታት ውስጥ ያልታየው ድርቅ በተከሰተባቸው የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች የሚኖሩ ሴቶችም በባህላዊ ልማዶችና ያልተመጣጠነ የሀብትና ሥልጣን ክፍፍል ምክንያት ድርቁ ከወንዶች በበለጠ ለስቃይ ዳርጓቸዋል።

በአፍሪካ ቀንድ ለስድስት ተከታታይ ወቅት ዝናብ ባለመጣሉ ምክንያት ድርቁ እጅግ ካየለባቸው የኢትዮጵያ አካባቢዎች አንዱ በሆነው የኦሮሚያ ክልል፣ ቦረና ዞን ፌሎ ቢቅ አካባቢ ነዋሪ የነበሩት ወይዘሮ ዳምቱ አብዱ ገልገሎ በድርቁ ምክንያት መተዳደሪያቸው የነበሩት ከብቶቻቸው አልቀዋል። በዚህም ምክንያት እርዳታ ፍለጋ ወደ ዱብሉቅ ወረዳ መሰዳቸውን ይገልፃሉ።

ልጆቼ ስምንት ናቸው። አራቱ ይማራሉ። እነዚህን ልጆች የማስተዳደርበት የለኝም። የማበላቸዉ የለኝም፤ መንግሥት እርዳታ ሲሰጠን አንድ ቀንለአምስት ሰዉ በሌላ ቀንደግሞ ለአራት ሰዉ በፈረቃ ያገኘነዉን ነዉ የምንቀምሰዉ። በድርቁ ምክንያት የተፈናቀሉ በየቀኑ ወደዚህ ወረዳ ይጎርፋሉ”

“ልጆቼ ስምንት ናቸው። አራቱ ይማራሉ። እነዚህን ልጆች የማስተዳደርበት የለኝም። የማበላቸዉ የለኝም፤ መንግሥት እርዳታ ሲሰጠን አንድ ቀንለአምስት ሰዉ በሌላ ቀንደግሞ ለአራት ሰዉ በፈረቃ ያገኘነዉን ነዉ የምንቀምሰዉ። በድርቁ ምክንያት የተፈናቀሉ በየቀኑ ወደዚህ ወረዳ ይጎርፋሉ” ያሉት ወይዘሮ ዳምቱ “አሁን በዚህ ወደዳ ሰፍረው ያሉት ብዙ ሰዎች ። በዚህ ወረዳ ስር አስራ ሶስት ቀበሌዎችአሉ። በተጨማሪም የአምስት ቀበሌ ላይ ነዋሪዎችተጨምረውባቸዋል። ስለሆነም የሚሰጠዉ እርዳታ ከሕዝቡ ቁጥር ጋር አይመጣጠንም፤ ብዙ ተቸግረናል።” ብለዋል።

ወይዘሮ ዳምቱ ለተከታታይ አምስት ወቅት ዝናብ ባለማግኘታቸው ያላቸውን ሁሉ አጥተዋል። ከሁሉም ሰቀቀን የሚሆንባቸው ግን ልጆቻቸውን የሚመግቡት ምግብ አለማግኘታቸው ነው። የችግሩ ስፋት የሚያሳድርባቸውን ስሜት ሲገልፁም "አንድ እናት በትንሹ ቡና ወይም ሻይ ማግኝት ትፈልጋለች። እንደ ቦረና ደግሞ የለመድነው ወተት ነው። አሁን እናቶች እና አዛዉንቶች ይህን ማግኘት አልቻሉም፤ድርቁ ከፍተኛ ጉዳት ነዉ ያደረሰዉ" ሲሉ አስረድተዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ድርቁ ይኖሩበት ከነበረው ኮሳ ቀበሌ ያፈናቀላቸው እና አሁን ዱብሉቅ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ያገኘናቸው ሌላዋ እናት ደግሞ ወይዘሮ ኤላማ ቦሩ ናቸው። እሳቸውም በድርቁ ምክንያት በተለይ ሴቶች ለከፍተኛ ችግር እና ጭንቀት መዳረጋቸውን ይገልፃሉ።

ሴቶች ብዙ ችግር አለባቸዉ ምክንያቱም ሚስት ናት፣ እንዲሁም እናትነች። ባል ከዉጭ ሲገባከእሷ ነዉ የሚጠብቀዉ፣ልጆችም ከእናት ነዉ የሚጠብቁት።ስለዚህም አሁን ባለዉ ሁኔታሴቶች ላይ ያለው ጫናከባድ ነዉ። አንድ በሆድ፣ሌላውን በጀርባ እንዲሁም አንድ አራት የሚሆኑ ደግሞ ከርሷ ጋር ቤት ይኖራሉ። እነዚህ ሁሉ ከእሷ ነው የሚጠብቁት። እናም በድርቁ እጅግ የተፈተኑ ሴቶች ናቸዉ።"

"ሴቶች ብዙ ችግር አለባቸዉ ምክንያቱም ሚስት ናት፣ እንዲሁም እናትነች። ባል ከዉጭ ሲገባከእሷ ነዉ የሚጠብቀዉ፣ልጆችም ከእናት ነዉ የሚጠብቁት።ስለዚህም አሁን ባለዉ ሁኔታሴቶች ላይ ያለው ጫናከባድ ነዉ። አንድ በሆድ፣ሌላውን በጀርባ እንዲሁም አንድ አራት የሚሆኑ ደግሞ ከርሷ ጋር ቤት ይኖራሉ። እነዚህ ሁሉ ከእሷ ነው የሚጠብቁት። እናም በድርቁ እጅግ የተፈተኑ ሴቶች ናቸዉ።"

በስልሳ ዓመታት ውስጥ ያልታየ እንደሆነ የተገልፀው አስከፊ ድርቅ ባጠቃቸው አካባቢ የሚኖሩ ማኅበረሰቦች አጣዳፊ ለሆነ የምግብ እና ውሃ እጥረት ቢዳረጉም፣ እንደ ወይዘሮ ዳምቱ እና ውይዘሮ ኤለማ ያሉ ሴቶች የሚደርስባቸው ተፅእኖ ግን እጅግ የከፋ ነው። ድርቁ ሴቶች በተለምዶ የተጣለባቸውን የቤተሰብ ኃላፊነት ሸክም እና የገንዘብ እጦት አባብሷል። በዚህም ምክንያት የሚቀጥለውን ምግብ ለመፈለግ እና ልጆቻቸውን ከሞት ለማዳን ረጅም ርቀት በእግራቸው ይጓዛሉ።

የሰባት ልጆች እናት የሆኑት ወይዘሮ ኤለማ ለምሳሌ አሁን የሚያድሩት ተጠልለው ባሉበት ድቡልቅ ወረዳ ውስጥ በሚገኝ ሜዳ ላይ ሲሆን እራሳቸውንም ሆነ ልጆቻቸውን ከጥቃት የሚጠብቁበት አቅም የላቸውም። የሚደረግላቸው መሰረታዊ የምግብ እርዳታም በቂ አይደለም። በተለይ የመጠጥ ዉሀ በሶስት ቀን አንዴ ብቻ የሚደርሳቸው በመሆኑ የውሃ ጥም ችግራቸው እዲቀረፍላቸው ይጠይቃሉ።

በዓለም ላይ በሚከሰቱ የተለያዩ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ ቀውሶች ወቅት ሴቶች ከወንዶች በበለጠ ተጠቂ እንደሚሆኑ የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ቀድሞም በሴቶች ላይ ተፅእኖ የሚያሳድሩ ባህላዊ ልማዶች የሚባባሱ በመሆኑ እንደሆነ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናችቸው አክሽን አጌንስ ሀንገር በተሰኘው ተቋም የኢትዮጵያ ወኪል ዳይሬክተር የሆኑት ሪያ ሩሶፎቦቪክ ይገልፃሉ።

"በብዙ ሀገሮች ሴቶች ተመጣጣኝ ባልሆነ ሁኔታ በረሃብ ይጎዳሉ። በዓለም ላይ ከሶስት ሀገራት በሁለቱ የሚኖሩ ሴቶች ከወንዶች በበለጠ በረሃብ እና በምግብ እጦት ሊሰቃዩ እንደሚችሉ እናውቃለን። ስለዚህ በአፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እንደ ውሃ እና እንጨት የመሳሰሉ ሀብቶችን ለማግኘት የሚደረገው ፉክክር ጨምሯል። ይህ ማለት ሴቶች ውሃ እና እንጨት ለማግኘት ረጅም ርቀት ይጓዛሉ። ይህ ደግሞ ለተለያዩ ጥቃቶች ያጋልጣቸዋል። እቤት ውስጥ የሚጠበቅባቸውን እንደ ልጅ መንከባከብ፣ ምግብ ማብሰል፣ ህመምተኞችን ወይም አዛውንትን መጠበቅ እና እርሻ ስራ ላይ ማገዝ የመሳሰሉ የዘወትር ስራቸውንም መስራት አይችሉም።"

በቦረና ዞን በተከሰተው አስከፊ ድርቅ ምክንያት ልጆቻቸውን መመገብ ያልቻሉ እናቶች ልጆቻቸውን ከሞት ለማትረፍ ምግብ ሊሰጧቸው የሚችሉ ሰዎች እንደሚሰጧቸው በስፍራው ያነጋገርናቸው እናቶች ሀዘን በሞላበት መንፈስ ነግረውናል። ሩሶፎቦቪክ እንደሚሉት በአንዳንድ ቦታዎችም ያለ እድሜ ጋብቻዎች ይፈፀማሉ።

"ጥናቶች እንደሚያሳዩት በአደጋዎች፣ ከፍተኛ በሆኑ የአየር ሁኔታ ክስተቶች እና የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትላቸው አደጋዎች ወቅት ሴቶች ያለአግባብ የበለጠ ለስቃይ ይዳረጋሉ። ለዚህ ምክንያቱ ያልተመጣጠነ የሀብት እና ሀይል ክፍፍል ነው። አሁን ለምሳሌ ጎጂ ልማዶች የምንላቸው እንደ ያለ እድሜ ጋብቻ መጨመሩን እያየን ነው።

ይሄ አንዳንዴ በቤተሰቡ ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ በሚል ይፈፀማል። እነዚህ ልጃገረዶች እድሜያቸው ገና በመሆኑ ለምግብ እጥረት የተጋለጡ ናቸው። የቤት ውስጥ ጥቃትም እንዲሁ መጨምሩን አይተናል።"

በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ እየተባባሰ መሄዱን ተከትሎ በዛ የሚኖሩ አርብቶ አደሮች በዘላቂነት ቤተሰቦቻቸውን መመገብ የሚችሉበት መንገድ ይፈልጋሉ። ሩሶፎቦቪክ እንደሚሉት የእርዳታ ተቋማትም የሚሰጡት እርዳታ በተለይ ሴቶች የሚደርስባቸውን ያልተመጣጠነ ተፅእኖ ከግምት ውስጥ ያስገባ እንዲሆን ጥረት እያደርጉ ነው።

"እኛ እንደ አክሽን አጌንስት ሀንገር እየረዳናቸው ያሉ በጣም የተጎዱ ሴቶች ያሉበትን ሁኔታ ለመቋቋም ሲጥሩ እናያቸዋለን። ረጅም ርቀት ተጉዘው ምግብ እና ውሃ በመፈለግ፣ እርዳታ በመፈለግ ለመቋቋም ይጥራሉ። ልጆቻቸውን ከግጭት እና ከድርቁ በተቻላቸው አርቀው ይዘው ሲሄዱ እናያቸዋለን። እኛም ሆንን ለሎች አጋር የእርዳታ ተቋማትም የአስቸኳይ ግዜ አደጋዎች ሁሉም ሰው ላይ በተመሳሳይ መንገድ ተፅእኖ እንደማያሳድሩ እና ሴቶች፣ በተለይ ደግሞ ልጃገረዶች የበለጠ ተጋላጭ መሆናቸውን እንገነዘባለን። ስለዚህም የእርዳታ ፕሮግራሞቻችንን ስንቀርፅ ያንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።"

ድርቁ በሴቶች ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ ከፍተኛ ቢሆንም፣ ለቤተሰባቸው ምግብ እና ውሃ የመፈለግ ወይም ልጆቻቸውን እርዳታ ወደሚገኝበት ስፍራ የመውሰድ ሀላፊነት አሁንም በሴቶች የሚያመዝን በመሆኑ እንደ ወይዘሮ ዳምቱ አብዱ እና ወይዘሮ ኤላማ ቦሩ ያሉ እናቶች ህይወታቸው እስካለ መፍጨረጨራቸውን ይቀጥላሉ።

XS
SM
MD
LG