በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም የሴቶች ቀን በመከበር ላይ ነው


ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በሃይደራባድ፣ ህንድ በተካሄደው የማራቶን ሩጫ ውድድር የተሳተፈች ታዳጊ
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በሃይደራባድ፣ ህንድ በተካሄደው የማራቶን ሩጫ ውድድር የተሳተፈች ታዳጊ

የዓለም የሴቶች ቀን ዛሬ ተከብሮ ውሏል፡፡ የዚህ ዓመት አከባበርም በጾታ እኩልነት ላይ ያተኮረ ሆኗል፡፡

ከእአአ 1911 ጀምሮ ላለፉት 112 ዓመታት ሲከበር የቆየው የዓለም የሴቶች ቀን በሴቶች መብት ትግልና በዓለም ዙሪያ ያሉ ሴቶች ያደረጉትን አስተዋጽኦ በማክበር ላይ ያተኩራል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለቀኑ የሰጠው ትኩረት ደግሞ በዲጂታል መስክ ወይም በኢንተርኔት ላይ የሴቶችንና የወጣት ልጃገረዶችን መብት ማስከበርና፣ በቴክኖሎጂ መስክ ያለውን የአቅርቦት ክፍተት መሙላት እንደሆነ ታውቋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከወንዶች ጋር ሲነጻጸር ለሴቶች ያለው የኢንተርኔት ተደራሽነት 259 ሚሊዮን ልዩነት ሲያሳይ፣ ደህንነትም አይሰማቸውም ሲል ተመድ ገልጿል፡፡ በዲጂታል መስክ ለመሳተፍም አስፈላጊውን ክህሎት ማግኘት አልቻሉም ብሏል፡፡

በዋሽንግተን ዲሲ፣ በዋይት ሃውስ ቤተ መንግሥት የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉና ከተለያዩ አገራት ለመጡ 11 ሴቶች የሽልማት ሥነ ሥርዓት ከጥቂት ሰዓታት በኋላ እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም አንድ ሽልማት በኢራን ላሉና የማሻ አሚኒን ግድያ ተቃውሞ ለመሩ ሴቶችና ወጣት ልጃገረዶች እንደሚበረከት ታውቋል፡፡

ከተሸላሚዎቹ አንዷ ኢትዮጵያዊቷ መዓዛ መሃመድ ስትሆን በጋዜጠኝነት ሥራዋ ጾታን መሠረት ባደረጉ ጥቃቶችና በቅርቡ በተካሄደው ጦርነት ወቅት በደረሰው የጾታ ጥቃት ላይ ትኩረት ባደረገው ሥራዋ ልትመረጥ መቻሏ ታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG