እናት ፓርቲ በአዲስ አበባ ከተማ ትላንት እሁድ የካቲት 26/2015 ዓ.ም ሊያካሂደው የነበረው ጠቅላላ ጉባዔ በክልከላ ምክኒያት በመስተጓጎሉ ለ3 ሚልየን ብር ኪሳራ መዳረጉን ገለፀ። ፓርቲው ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የጠራቸውን አባላቱን ጨምሮ 700 ሰው መጉላላት እንደደረሰበት አስታውቋል።
ፓርቲው ጠቅላላ ጉባዔውን ለማካሄድ የአዳራሽ ውል ስምምነት ፈጽሞ የነበረው ቅድስተ ስላሴ ዩኒቨርሲቲ ከተባለ ተቋም ጋር እንደነበር ገልፆ በስብሰባው ሰዓት ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው በሚል ወደ ውስጥ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ ከተቋሙ ምላሽ ለማድረግ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተወካዮች የፓርቲውን ጉባዔ ለመታዘብ በቦታው እንደነበቱ የገለፀልን ኮምዩኒኬሽን ቦርዱ ጉዳዩን እየተከታተለው መሆኑን አስታውቋል።
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡