በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግሥታቱ ድርጅት ኤርትራን በሰብአዊ መብት አያያዟ ከሰሰ ኤርትራ ውንጀላውን ውድቅ አደረገች


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኤርትራ ‘ይታያል’ ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝ አስመልክቶ የሃገሪቱን መንግሥት ከሰሰ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኤርትራ ‘ይታያል’ ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝ አስመልክቶ የሃገሪቱን መንግሥት ከሰሰ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኤርትራ ‘ይታያል’ ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝ አስመልክቶ የሃገሪቱን መንግሥት ከሰሰ። “አሳሳቢነቱ ቀጥሏል፣ መሻሻል አይታይበትም” ሲልም በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው መግለጫ ተችቷል።

የኤርትራ መንግሥት በበኩሉ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው ምላሽ፡ ”ከጠላትነት አጀንዳቸው የመነጨ” ያለው ድርጊት መቀጠሉን ጠቅሶ ድርጅቱን ወንጅሏል።

UN Deputy High Commissioner for Human Rights @NadaNashif told the Human Rights Council during a dialogue on the human rights situation in #Eritrea that it "remains dire."She urged Eritrea to step up engagement with @UNHumanRights.STATEMENT ▶️ https://t.co/jcF4v9t4u6 pic.twitter.com/oDWe1ca4Mn

— UN Human Rights Council 📍#HRC52 (@UN_HRC) March 6, 2023

“በኤርትራ ያለው የሰብአዊ መብት አያያዝ አሳሳቢ ከመሆኑም በላይ ምንም መሻሻል አይታይበትም።” ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ኮምሽነር አስታወቀ።

ኮምሽነሩ አያይዞም፡ “ማሰቃየት፣ የዘፈቀደ እስር፣ በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች ኢሰብአዊ አያያዝ፣ ደብዛ መጥፋት ወይም የገቡበት ያለመታወቅ እና እንዲሁም ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የመሰብሰብ እና በሰላማዊ መንገድ የመሰብሰብ መብቶችን የሚገድቡ እርምጃዎችን ጨምሮ ስር የሰደደ የሰብአዊ መብት ረገጣ መቀጠሉን የሚያረጋግጡ አስተማማኝ መረጃዎች ጽህፈት ቤታችን እየደረሰን ነው።” ብሏል።

“በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ለአስርት ዓመታት ታስረው እንደሚገኙ ሪፖርቶች ይጠቁማሉ። በተጨማሪም

በእምነታቸው የተነሳ ሰዎች በዘፈቀደ ለእስር መዳረጋቸው እና መዋከባቸው እንደቀጠለ ሲሆን፤ በዚህም ሳቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሃይማኖት መሪዎች እና ተከታዮቻቸው ላይ የሚደርሰው በደል መቀነስ አላሳየም፤” ሲል ወንጅሏል።

“በዚያች አገር የሚካሄደው የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ኤርትራውያን ሃገራቸውን ጥለው የሚሰደዱበት ዋነኛው ምክንያት ነው” ያለው ሪፖርት፡ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2022 መገባደጂያ ከ160 ሺህ በላይ ጥገኝነት ጠያቂዎች በኢትዮጵያ፣ ከ130 ሺህ በላይ ስደተኞች ደግሞ በሱዳን መኖራቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት ከፍተኛው የስደተኞች ኮምሽነር ዋቢ በማድረግ ጠቁሟል።

“ይህም በተለይ ከ18 እስከ 49 አመት ባለው የእድሜ ክልል ካለፉት ዓመታት ከነበረው በመጠኑ መጨመሩን ያሳያል።” ብሏል።

በቅርቡም አንዳንድ አገሮች ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን አስገድደው ወደ አገራቸው በመመለስ ላይ መሆናቸውን የሚጠቁሙ ሪፖርቶች እየወጡ መሆናቸውን አውስቶ፣ ይህም ከስደት ተመላሾችን በሃገራቸው ለሚጠብቃቸው ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ያጋልጧል።” ሲል አስጠንቅቋል

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ኮምሽነር 52ተኛ ስብሰባ ላይ የተገኘው የኤርትራ ልዑካን ቡድን ጉዳዩን አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር በድረ ገጹ እንዲህ አስነብቧል።

Statement of #Eritrean Delegation at UNHRC 52nd Session "The unrelenting harrasment of Eritrea for more than ten years now through unwarranted appointment of Special Rapporteurs stems from, & is inextricably linked with, hostile agenda of its detractors"https://t.co/udfdz5Hx1G pic.twitter.com/Uj6PYNZlRe

— Yemane G. Meskel (@hawelti) March 6, 2023

“ከአስር ዓመታት በላይ ያስቆጠረው በኤርትራ ላይ የሚፈጸው የማያባራ ትንኮሳ፣ አሁን ደግሞ ማንም ያልጠየቀው እና ሚዛን የጎደለው ትችት የሚሰነዝር ልዩ መርማሪ ቡድን መሰየም፣ ከጠላትነት አጀንዳቸው የመነጨው ድርጊት ቀጥሏል።” ሲል ከሷል።

መግለጫው አክሎም፡ “እንደ እውነቱ ከሆነ፣ ህወሃት በህዳር 2020 ጦርነት ከከፈተበት ጊዜ አንስቶ፤ የልዩ መርማሪው ያለፉት ሁለት ዓመታት ዋና ትኩረት፣ ትልቁን ተልኮውን ለማስፈጸም በተቀመጠለት አጀንዳ መሰረት ኤርትራን መወንጀል ነው።” ብሏል።

“እንደሚታወሰው ልዩ መርማሪው ባለፈው ዓመት ባወጣው ዘገባ በኤርትራ እና በሶማሊያ መንግሥታት መካከል በተደረገ የሁለትዮሽ ሥምምነት መሰረት በኤርትራ ወታደራዊ ሥልጠና ሲወስዱ የነበሩትን 5 ሺ ሶማሊያውያን በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት አሰማርታለች” ሲል ኤርትራን በሃሰት ከሷል።” ሲል ተችቷል።

XS
SM
MD
LG