ምርጫውን ተከትሎ በርካታ በውጤቱ የተቆጡም ደስታውቸውንም እየገለጡ ያሉ ዜጎች እንዳሉ የተናገሩት በናይጄሪያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ውዝግቡ ሙግቶች በህጋዊ ሂደት ውሳኔ እስኪያገኝ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አምባሳደር ሜሪ ቤት ሌነርድ “የምርጫ ሂደት ፍርድ ቤት ደረጃ ሲደርስ ላያመረቃ ይችላል፡፡ ነገር ግን በህግ የበላይነት በሚመራ ህገ መንግሥታዊ ዲሞክራሲ ትክክለኛው አሰራር እርሱ ሊሆን ይችላል” ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ነጻው የናይጄሪያ የምርጫ ኮሚሽን በፕሬዚደንታዊ ምርጫው ቦላ አህመድ ቲኑቡ ማሸነፋቸውን አውጇል፡፡
“ምርጫው ተጨበርብሯል” ያሉት ተቃዋሚ መሪዎች በበኩላቸው በፍርድ ቤት እንሟገታለን ብለዋል፡፡