በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁለት የቀይ መስቀል ሰራተኞች ማሊ ውስጥ ታገቱ


ጋኦ፣ ማሊ
ጋኦ፣ ማሊ

የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ሁለት ሰራተኞች ቅዳሜ ማሊ ውስጥ ታፍነው መወሰዳቸውን የድርጅቱ የማሊ ቅርንጫፍ በትዊተር ገፁ አስታውቋል።

የሰራተኞቹን መታገት ያረጋገጡት የቅርንጫፍ መሰሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አሚናታ አልሳኔ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደገለፁት፣ ድርጊቱ የተፈፀመው ከጋኦ ወደ ኪዳል በሚወስደው መንገድ ላይ ነው።

እ.አ.አ ከ2012 ጀምሮ ማሊ በከፍተኛ የፀጥታ ችግር ውስጥ የገባች ሲሆን፣ የውጭ ዜጎችን እና ማሊያውያንን ማገትን ጨምሮ በርካት ሁከቶች እየተለመዱ መጥተዋል።

በጥር ወር አንድ የዓለም ጤና ድርጅት ሰራተኛ የሆነ ዶክተር ታግቶ ከአንድ ወር በኃላ ተለቋል። ባለፈው አመት ግንቦት ወር ላይም በተመሳሳይ ታጣቂዎች ሶስት የጣሊያን እና አንድ የቶጎ ዜግነት ያላቸውን ዜጎች በደቡብ ምስራቅ የማሊ ክፍል ማገታቸው ይታወሳል።

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ ሰራተኞቹ እንዲለቀቁ ጠይቋል።

XS
SM
MD
LG