በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የሮሂንጋ ስደተኞችን ቤት አልባ አደረገ


የሮሂንጋ ስደተኞች ባንግላዲሽ በሚገኘው መጠለያ ጣቢያቸው የተነሳው እሳት መኖሪያዎቻቸውን ሲያቃጥል ይመለከታሉ - መጋቢት 5፣ 2023
የሮሂንጋ ስደተኞች ባንግላዲሽ በሚገኘው መጠለያ ጣቢያቸው የተነሳው እሳት መኖሪያዎቻቸውን ሲያቃጥል ይመለከታሉ - መጋቢት 5፣ 2023


በደቡብ ምስራቅ ባንግላዲሽ፣ ከሚየንማር የተፈናቀሉ የሮሂንጋ ስደተኞች በሚኖሩበት መጠለያ ጣቢያ የተነሳው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ቤት አልባ እንዳደረጋቸው ባለስልጣናት አስታወቁ።

የባንግላዲሽ ምክትል የስደተኞች ኮሚሽነር የሆኑት ሻምሱድ ዱዛ እንደተናገሩት ባሉካሊ በተሰኘው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በአባዛኛው ከቀርከሃ እና ላስቲክ የተሰሩ ቢያንስ አንድ ሺ የሚሆኑ መኖሪያዎች በእሳቱ ወድመዋል።


ባለስልጣናቱ በእሳቱ የደረሰው ጉዳት መጠን እስካሁን አለመታወቁን ገልፀው፣ በርካታ ሰዎችን ግን ደህንነታቸው ወደሚጠበቅበት ስፍራ መውሰዳቸውን ቢያስታውቁም፣ አንዳንድ ስደተኞች ግን የቤተሰባቸው አባላት እንደጠፉባቸው እየገለፁ ነው።

ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ ይህ ሶስተኛው ከባድ ቃጠሎ ነው። እ.አ.አ በ2021 በደረሰ የእሳት አደጋ ቢያንስ 15 ሰዎች ሲገደሉ 50ሺህ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ቤት ለቀናት ቤት አልባ ሆነው ነበር። በተመሳሳይ ያለፈው መጋቢት ወር የተነሳ ከባድ የእሳት ቃጠሎ የአንድ ታዳጊ ሕፃን ህይወት አጥፍቶ ወደ 2ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን ደግሞ ቤት አልባ አድርጓል።


እ.አ.አ በ2017 የፀጥታ ኃይሎች እና የቡዲስት ታጣቂዎችን ያካተተውን ጥቃት የሸሹ ቢያንስ 740 ሺህ የሮሂንጋ ሙስሊሞች ወደ ተጨናነቀው የባንግላዲሽ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ መግባታቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG