በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ዩክሬንን ጎበኙ


የሩሲያው መከላከያ ሚኒስትር በዩክሬን ጉብኘት አድርገዋል
የሩሲያው መከላከያ ሚኒስትር በዩክሬን ጉብኘት አድርገዋል

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ፣ በዩክሬን ደቡባዊ ግዛት ዳኔትስክ፣ በምስራቅ እዝ አዲስ ከተቋቋሙት ወታደራዊ እዞቹ ውስጥ አንዱ የሆነውን አጥቂ ጦራቸውን፣ ዛሬ ቅዳሜ፣ በስፍራው ተገኝተው መጎብኘታቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ በማህበራዊ ሚዲያ መልዕክት ማስተላለፊያ ቴሌግራም ላይ ዛሬ ባወጣው የቪዲዮ መልዕክት ለሩሲያ ወታደራዊ ኃይሎች የሚዳይ ሽልማት ሲሰጡ አሳይቷል፡፡

ሾይጉ ሩሲያ ዩክሬን ውስጥ ባሳየቸው ደካማ የጦር እንቅስቃሴ ሲተቹ እንደነበር ተመልክቷል፡፡

የእንግሊዝ የመከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ዩክሬን ውስጥ የዶናባስ ክልል ከተማ በሆነችው ባክሙት አካባቢ የተፋፋመ ውጊያ መኖሩን አስታውቋል፡፡

በባክሙት የሚገኘው ድል በዙሪያው ያለውን የዶባንስ ክልል ለመያዝ ለሚደረገው ስትራቴጂ ጥሩ መወጣጫ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

ዩክሬን ከተማዪቱ መጠነኛ ስትራቴጂክ ጠቀሜታ ቢኖራትም በዚያ ስፍራ የሚከፈለው ከፍተኛ ኪሳራ የጦርነቱን ሂደት በመወሰን ትልቅ ስልፍራ ሊኖረው እንደሚችል አስታውቃለች፡፡

የብሪታኒያው የስለላ ድርጅት፣ የሩሲያ ጦር በሶስት አጥቃጫዎች ለጥቃት የተጋለጠ ሲሆን፣ ዩክሬን ግን ልዩ ኃይሎችዋን በማስማራት አካባቢዎቹን በከፍተኛ ደረጃ እያጠናከረች ነው ብሏል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለንስኪ ትናንት ዓርብ ከበርካታ አካላት ጋር በተደረጉ ስብሰባዎችና ድርድሮች ላይ መሳተፋቸውን ትናንት ባሰሙት እለታዊ የምሽት ንግግራቸው፣ ተናግረዋል፡፡

የስብሰባዎቻቸው ዋና ትኩረት ሩሲያ ለፈጸመችው ድርጊት ተጠያቂ እንድትሆን ማድረግ ነው ያሉት ዜለንስኪ “ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት የሩሲያ ጦር ወንጀለኞች የሚቀጣ መሆኑን ለማረጋገጥ የቻልነውን ሁሉ እያደረግን ነው” ብለዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን አዲስ ወታደራዊ እርዳታ እንደምትሰጥ ትናንት አርብ ያስታወቀች ሲሆን፣ ይህም በድምሩ ወደ 400 ሚሊዩን ዶላር የሚደርስ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን አስታውቀዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በቅርቡ የምትስጠውን ጥቅል ወታደራዊ እርዳታ ጨምሮ እስካሁን ለዩክሬን ከ32 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወታደራዊ እርዳታ መስጠቷ ተመልክቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴት ጠቅላይ አቃቢ ህግ ሜሪክ ጋርላንድ ዩክሬን ውስጥ በተካሄደው የፍትህና የጦር ወንጀሎች ጉባኤ ላይ ለመገኝት ትናንት አርብ በዩክሬን ድንገተኛ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ስብሰባውን አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስ ፍትህ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ፣ ጋርላንድ በምዕራባዊ የዩክሬን ውስጥ ለቪቭ ከተማ በተካሄደው ጉባኤ በመገኘት “ሩሲያ በሉአላዊ ጎረቤት አገር ላይ ለፈጸመቻቸው ወንጀሎችና ፍትሃዊና ምክንያታዊ ላልሆነ ወረራዋ ተጠያቂ ለማድረግ ያለንን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ በርካታ ስብሰባዎችን አካሂደዋል” ብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG