የናይጄሪያ የተቃዋሚው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እጩዎች የገዥውን ፓርቲ እጩ አሸናፊ ያደረገውን የምርጫ ውጤት እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል፡፡ የቅዳሜው ምርጫ በቴክኒክ እና የምርጫ ሠራተኞች ችግር ገጥሞት የነበረ ሲሆን በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ መስጠቱ ለአንድና ከዚያ በላይ ለሆነ ቀን ዘግይቷል፡፡
የናይጄሪያው የምርጫ ኮሚሽን፣ ትናንት ረቡዕ የገዥው ኦል ፕሮግሬሲቭ ኮንግረንስ ፓርቲ፣ እጩ የሆኑት ቦላ አህመድ ቲኑቡ የቅዳሜው ምርጫ አሸናፊ መሆናቸውን ካስታወቀ ጥቂት ሰዐታት በኋላ የሠራተኞች ፓርቲ ከጋዜጠኞችና ከደጋፊዎች ጋር ተገናኝቷል፡፡
የሠራተኛው ፓርቲ ፕሬዚዳንታዊ እጩ ፒተር ኦቢ በረቡዕ ስብሰባ ላይ ባይገኙም የሳቸው ምክትል ዩሱፍ ዳቲ አህመድ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ እሳቸውና ኦቢ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤቱን በፍርድ ቤት እንደሚሞግቱ አስታውቀዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡