በዓሉ በየዓመቱ በሚከበርበት ምኒልክ አደባባይ፣ ከፖሊስ ጋራ ግጭት ተፈጥሮ ፖሊስ በዓል ለማክበር የተሰበሰበውን ሕዝብ በአስለቃሽ ጭስ ሲበትን ታይቷል።
ሕዝቡ ወደ አደባባዩ እንዳይገባ እና ወደ ሐውልቱ እንዳይቀርብ ፖሊስ ክልከላ ሲያደርግም እንደ ነበረ አስተያየታቸውን የሰጡን ግለሰቦች ተናግረዋል፡፡
አስለቃሽ ጭስ መተኮሱን ተከትሎ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አስተያየት ሰጪዎች ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል፣ በዓሉ በመስቀል አደባባይ በተለያዩ ዝግጅቶች ደምቆ ተከብሯል፡፡ በሥፍራው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ፣ “ዓለም ያከበረውን የዓድዋ ድል እኛም ከዚያ በላይ ማክበር አለብን፤” ብለዋል። አክለውም “አብሮ ከመኖር ይልቅ በሚከፋፍለን ጉዳይ ላይ ብቻ መንጠላጠል ብዙ ርቀት ላይወስደን ይችላል፤” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡