በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጄሪያ የተቃዋሚው እጩ የምርጫውን ውጤት በፍ/ቤት ሊሞግቱ ነው


በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሦስተኛ ደረጃን ያገኙት ፒተር ኦቢ
በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሦስተኛ ደረጃን ያገኙት ፒተር ኦቢ

በናይጄሪያ ባለፈው ዓርብ በተደረገውና ከፍተኛ ፉክክር በታየበት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሦስተኛ ደረጃን ያገኙት ፒተር ኦቢ ውጤቱን ባለመቀበል ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስዱ አስታውቀዋል፡፡

ለፖለቲካው ፉክክር አዲስ የሆኑት የሰራተኛ ፓርቲው ኦቢ 6.1 ሚሊዮን ድምጽ በማግኘት የሦስተኛ ደረጃን ሲያገኙ፣ ለሁለት ዓመታት በሁለት ፓርቲዎች ተጽእኖ ስር የነበረው የናይጄሪያ ፖለቲካ መድረክ ላይ አዲስ የፖለቲካ ሰው ብቅ ያሉ መስሎ ነበር፡፡

“መብታችንን ለማስከበር ሁሉንም ሕጋዊ አማራጮችን እንጠቀማለን” ሲሉ ተደምጠዋል ኦቢ፡፡

በናይጄሪያ ምርጫ የገዢው ፓርቲ ወኪልና የቀድሞ የሌጎስ አገረ ገዢ ቦላ ቲኑቡ 8.8 ሚሊዮን በማግኘት አሸናፊ መሆናቸው ትናንት ረቡዕ ይፋ ተደርጓል፡፡ ወንበራቸውን በመጪው ግንቦት ይረከባሉ ተብሏል፡፡

ተቃዋሚዎች ቅሬታቸውን ፍ/ቤት ለማቅረብ የ 21 ቀን ግዜ አላቸው፡፡

በአፍሪካ ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ባላት ናይጄሪያ የተደረገው ምርጫ በአጠቃላይ ሰላማዊ ቢሆንም፣ በምርጫ ጣቢያዎች ረጅም መዘግየት መታየቱና በኢንተርኔት አማካይነት ሲታወጅ የነበረው ውጤት እያዘገመ መምጣት ድምጽ ሰጪዎችን ሲያበሳጭ፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ደግሞ ማጭበርብር ተከሰቷል በሚል ወደ ክስ በማምራት ላይ ናቸው፡፡

XS
SM
MD
LG