በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤድስ ፕሮግራሙ የ25 ሚሊዮን ሰዎችን ሕይወት ታድጓል ተባለ


የኤድስ ፕሮግራሙ የ25 ሚሊዮን ሰዎችን ሕይወት ታድጓል ተባለ
የኤድስ ፕሮግራሙ የ25 ሚሊዮን ሰዎችን ሕይወት ታድጓል ተባለ

የዩናይትድ ስቴተስ የኤድስ ፕሮግራም የ25 ሚሊዮን ሰዎች ሕይወትን ታድጓል ሲሉ የፕሮግራሙ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ጆን ንኬንጋሶንግ አስታውቀዋል።

‘የፕሬዚዳንቱ የአስቸኳይ ግዜ ፕላን ለኤድስ’ ወይም ፔፕፋር በሚል ምጻረ ቃል የሚታወቀው ፕሮግራም በፕሬዚዳንት ጆርጅ ዎከር ቡሽ አስተዳደር ከ20 ዓመታት በፊት የተቋቋመ ሲሆን በኤድስ ላይ የሚደረገውን ዘመቻ እጅግ ረድቷል ሲሉ ደቡብ አፍሪካን በመጎብኘት ላይ ያሉት የፕሮግራሙ ኃላፊ ተናግረዋል።

“የ25 ሚሊዮን ሠዎችን ሕይወት አትርፏል፣ 5.5 ሚሊዮን ሕጻናት ከኤችአይቪ/ኤድስ ነጻ ሆነው ተወልደዋል፣ የጤና ሥርዓቶችም አስደናቂ መሻሻል አሳይተዋል” ብለዋል ኃላፊው ጆን ንኬንጋሶንግ።

ለፕሮግራሙ ከተመደበው 110 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ 95 በመቶ የሚውለው በበሽታው በጣም ለተጠቃችው አፍሪካ ነው ሲሉ አክለዋል ኃላፊው።

ፕሮግራሙ 20 ሚሊዮን ለሚሆኑ አፍሪካውያን ሕይወት አድን መድሃኒት እንደሚያቀርብ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG