በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጣሊያን የጀልባ አደጋ የሞቱት ፍልሰተኞች ቁጥር በመጨመር ላይ ነው


ባለፈው እሁድ በደቡብ ጣሊያን ባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን በያዘ ከእንጨት የተሠራ ጀልባ ላይ በደረሰው አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 64 አሻቅቧል ተብሏል።
ባለፈው እሁድ በደቡብ ጣሊያን ባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን በያዘ ከእንጨት የተሠራ ጀልባ ላይ በደረሰው አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 64 አሻቅቧል ተብሏል።

ባለፈው እሁድ በደቡብ ጣሊያን ባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን በያዘ ከእንጨት የተሠራ ጀልባ ላይ በደረሰው አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 64 አሻቅቧል ተብሏል። ጀልባው ከቋጥኝ ጋር ተጋጭቶ 12 ሕጻንትን ጨምሮ ቢያንስ 64 መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ቢያንስ አንድ አስከሬን ከባህሩ ውስጥ ትናንት ሰኞ ተጉትቶ መውጣቱን የዜና ማሰራጫዎች ዘግበዋል።

ከአደጋው የተረፉት እንደሚሉት ከቀናት በፊት ከቱርክ በተነሳችው ጀልባ ላይ ከ150 እስከ 200 የሚሆኑ ፍልሰተኞች ተሳፍረው ነበር።

አንድ ቱርካዊና ሁለት የፓኪስታን ዜጎች ሰዎችን በሕገ ወጥ መንገድ በማስተላለፍ ተጠርጥረው ተይዘዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

ወደ አውሮፓ ሲሻገሩ የነበሩትን ፍልሰተኞች የያዘው ጀልባፍርስራሽ በደቡብ ጣሊያን ባህር ዳርቻ ትናንት ሰኞ ሲንሳፈፍ ተገኝቷል። እንጨት፣ የጋዝ ጀረኪና፣ የምግብ መያዣና የሕጻናት አሻንጉሊቶች ከፍርስራሹ ጋር ከታዩት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የአንድ ወር ብቻ ዕድሜ ያለው ሕጻን ከአደጋው ከተረፉትና ቀድመው ከተገኙት መካከል አንዱ ነው ተብሏል፡፡

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት 2022፣ 105 ሺህ የሚሆኑ ፍልሰተኞች ባህሩን አቋርጠው ጣሊያን ገብተዋል። አብዛኞቹ ከአፍሪካ መካከለኛው ምሥራቅ እና ደቡብ እስያ መሆናቸውም ታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት የጠፉ ፍልሰተኞች ፕሮጀክት እንደሚለው ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ 220 ፍልስተኞች በሜዲትሬኒያን ባህር ላይ ሕይወታቸውን አጥተዋል አልያም ጠፍተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG