በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ እየመረጠች ነው


በካኖ የምርጫ ጣቢያ መዘግየት የተበሳጩ መራጮች (ፎቶ ሮይተርስ የካቲት 25, 2023)
በካኖ የምርጫ ጣቢያ መዘግየት የተበሳጩ መራጮች (ፎቶ ሮይተርስ የካቲት 25, 2023)

ናይጄሪያውያን ፕሬዝደንታቸውን ለመምረጥ ዛሬ ድምጽ ሲሰጡ ውለዋል። በምርጫው ሶስት ዕጩዎች ሥልጣኑን ለመያዝ ተቀራራቢ ፉክክር በማድረግ ላይ ናቸው።

በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች መዘግየትና ቴክኒካዊ ችግር ታይቷል በማለት ድምጽ ሰጪዎች ቅሬታቸውን እያሰሙ እንደሆነ የኤ.ኤፍ.ፒ ዘገባ አመልክቷል።

ለድምጽ ሰጪዎች ሊሰራጭ ነበር ያለውን ግማሽ ሚሊዮን ዶላር ከአንድ ተቃዋሚ ፓርቲ የምክር ቤት አባል ላይ መያዙን ፖሊስ ትናንት አስታውቋል። ቺንዬሬ ኢግዌ ከተባሉ የምክር ቤት ዓባል ቦርሳ ውስጥ 498 ሺህ 100 ዶላርና፣ ገንዘቡ የሚሰራጭበትን ዝርዝር የያዘ ሰነድ መያዙን ያስታወቀው ፖሊስ፣ ከአንድ ሌላ ተጠርጣሪ ደግሞ 70 ሺህ 300 ዶላር የሚገመት ገንዘብ በአገሪቱን መገበያያ ገንዘብ ናያራ መያዙን አስታውቋል። ይህም ገንዘብ ድምጽ ለመግዣ ሊውል እንደነበር ተጠርጥሯል ሲል ፖሊስ ይገልጻል።

90 ሚሊዮን የሚሆኑ ድምጽ ሰጪዎች ባሏት ናይጄሪያ፣ አዲሱ ፕሬዝደንት አገሪቱን ከተባባሰው የጸጥታ ችግር፣ የኢኮኖሚ ቀውስና ድህነት እንዲታደግላቸው ዜጎቿ ይሻሉ።

ናይጄሪያ ከወታደራዊ አገዛዝ ነጻ ከሆነችበት እ.አ.አ 1999 ወዲህ፣ ከሁለት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ውጪ ለመጀመሪያ ግዜ ተሰሚነት ያለው ሶስተኛ እጩ ብቅ ብሏል። የሠራተኛ ፓርቲው ተወካይ የሆኑት 61 ዓመቱ ፒተር ኦቢ በወጣቶች ዘንድ ተሰሚነትን አግኝተዋል።

የተሰናባቹ ፕሬዝደንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ፓርቲ የሆነው ‘ኦል ፕሮግረሲቨ ኮንግረስ’ እና ተቀናቃኙ ‘ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ፖርቲ’ የናይጄሪያን ፖለቲካ በበላይነት ተቆጣጥረውት ከርመዋል። ፒትር ኦቢ ከሁለቱ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ከፍተኛ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

XS
SM
MD
LG