በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያውያን ከቀጣዩ ፕሬዚዳንት ምን ይጠብቃሉ?


ናይጄሪያውያን ነገ ቅዳሜ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያካሂዳሉ።
ናይጄሪያውያን ነገ ቅዳሜ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያካሂዳሉ።

ናይጄሪያውያን ነገ ቅዳሜ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያካሂዳሉ። የአሜሪካ ድምጽ የሀውሳ ቋንቋ ክፍል ናይጄሪያውያን ሀገራቸው ያለችበትን ሁኔታ በተመለከት ምን ተስፋ እና ሥጋት እንዳላቸው ጠይቋል።

የዛምፋራ ክፍለ ግዛት ነዋሪው ሙስታፋ የጸጥታ መደፍረሱ ጉዳይ በቀዳሚነት መፍትሄ ሊፈልግለት እንደሚገባ ተናግሯል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ዩኤንኤችሲአር እንዳስታወቀው በሀገሪቱ ባለው ብጥብጥ ምክንያት 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን ህዝብ ለአገር ውስጥ ተፈናቃይነት ተዳርጓል። 343 ሺህ ሰዎች አገር ጥለው ተሰድደዋል።

በጽንፈኛ ቡድኖች ሁከት፣ በማኅበረሰቦች የእርስ በርስ ግጭት እና ማስለቀቂያ ለማስከፈል በሚፈጸመው ጠለፋ ምክንያት የሀገሪቱ ፀጥታ እና መረጋጋት አሽቆልቁሏል።

የሚመረጡት ፕሬዚዳንት በመጀመሪያ ለጸጥታው ጉዳይ በማስከተል ደግሞ ለረሃቡ መላ እንዲፈልጉ እፈልጋለሁ ያሉት ሙስጠፋ አቡበከር የረሃቡ መንስዔ ብጥብጡ ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG