በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ ማስተርካርድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዓለም ባንክን እንዲመሩ ታጩ


ወርልድ ባንክን እንዲያስተዳድሩ የታጩት የማስተርካርድ ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አጄይ ባንጋ
ወርልድ ባንክን እንዲያስተዳድሩ የታጩት የማስተርካርድ ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት አጄይ ባንጋ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የቀድሞ ማስተርካርድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አጄይ ባንጋ የዓለም ባንክን እንዲመሩ በእጩነት አቅርበዋል።

አጄይ ባንጋ የሥልጣን ዘመናቸው ከመጠናቀቁ አንድ ዓመት ቀደም ብለው ሥራቸውን የሚለቁትን ዴቪድ ሚልፓስን ይተካሉ። ዴቪድ ሚልፓስ ነዳጅን ለማግኘት ቅሪተ አካልን ማቃጠል የከባቢ አየርን ሙቀት ይጨምራል የሚለውን ሳይንስ በጥርጣሬ በመጠየቃቸው ምክንያት የሥራ ዘመናቸው እንድ ዓመት እየቀረው እንደሚለቁ ታውቋል።

አጄይ ባንጋ በአንድ የግል መዋዕለ ንዋይ አስተዳዳሪ ኩባንያ ከፍተኛ ኃላፊ ሲሆኑ፣ ከዚህ ቀደም ደግሞ ማስተርካርድ የተሰኘው አበዳሪ ኩባንያ ኃላፊ ነበሩ።

ባንጋ “የግልና የመንግስት ሃብቶችን በማንቀሳቀስ የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ ወቅታዊ የዓለማችንን ችግሮች ለመስፍታ ተፈላጊው ልምድ አላቸው” ሲሉ ባይደን ተናግረዋል።

የአሜሪካ የግምጃ ቤት ሃላፊ ያኔት የለን ባወጡት መግለጫ ደግሞ፣ የባንጋ ልምድ የዓለም ባንክ ግቦች የሆኑትንና “አስከፊ ድህነትን ማጥፋትንና ብልጽግናን ማዳረስ“ የሚሉትን ከዳር ለማድረስ ያግዛቸዋል ብለዋል።

እንደልማድ ሆኖ አሜሪካ የዓለም ባንክ ሃላፊን ታጫለች። ባንጋ ቦታውን የሚያገኙ ከሆነ፣ በህንድ የተወለዱ የመጀመሪያው የባንኩ መሪ ይሆናሉ።

XS
SM
MD
LG