ፊንላንድ ለዪክሬን ሶስት ሌፐርድ እና ሁለት ታንኮችን ጨምሮ የ169 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ እንደምትልክ ገለጸች፡፡
የፊንላንድ የመከላከያ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ የሚላኩት ታንኮች የተቀበሩ ፈንጂዎችን ማስወገድ የሚችሉ መሆናቸውን ጠቅሶ የሚላከው የገንዘብ ድጋፍም ታንኮቹን ስራ ላይ ለማዋል እና ለእድሳት የሚያስፈልገውን ወጪ ያካተተ መሆኑን ጠቅሟል፡፡
ስፔን ስድስት ሌፐርድ ሁለት ታንኮችን ለዩክሬን እንደምትልክ ትናንት አስታውቃለች፡፡
ታንኮቹ እየተላኩ ያሉት የዩክሬን ባለስልጣናት የሩስያ ኃይሎችን ጥቃት ለመመከት ጀርመን ሰራሾቹ ሌፐርድ ታንኮች እንዲላኩላቸው ባቀረቡት ተማጽኖ መሰረት መሆኑ ተመልክቷል፡፡
ጀርመን መጀመሪያ ላይ ጦርነቱ እንዲባባስ ያደርጋል በሚል ስጋት ታንኮቹ አንዲላኩ ከመፍቀድ ተቆጥባ የነበረ ቢሆንም ታንኩ ያላቸው አጋሮቿ ግን መላክ ይችላሉ ብላ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
ጦርነቱን በሚመለከት ዛሬ የብሪታኒያ የመከላከያ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ የሩስያ ኃይሎች ዶኔትስክ ውስጥ በሚገኘው ቩህሌዳር በተባለው አካባቢ ካሁን ቀደም ብርቱ ሽንፈት ያገኛቸው ቢሆንም እንደገና አዲስ ጥቃት ሊከፍቱ እየተዘጋጁ ሳይሆኑ እንደማይቀሩ ተናግሯል፡፡