በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጂቡቲ ዓርብ ምርጫ ይካሄዳል፣ ዋናው ተቃዋሚ አይሳተፍም


እ.አ.አ በ2016 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ በጅቡቲ ከተማ የሚገኝ የምርጫ ጣቢያ ድምፅ ሲቆጠር ይታያል። በመጪው አርብ በሚካሄደው የፓርላማ ምርጫ፣ የጅቡቲ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ ራሱን አግልሏል።
እ.አ.አ በ2016 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ በጅቡቲ ከተማ የሚገኝ የምርጫ ጣቢያ ድምፅ ሲቆጠር ይታያል። በመጪው አርብ በሚካሄደው የፓርላማ ምርጫ፣ የጅቡቲ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ ራሱን አግልሏል።

ጂቡቲያውያን ዓርብ የፓርላማ አባላትን ይመርጣሉ። ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ ግን ምርጫው የተጭበረበረ ነው በሚል ራሱን አግልሏል፡፡

65 መቀመጫ ላላው ፓርላማ የሚወዳደሩት ሁለት ፓርቲዎች ብቻ ሲሆኑ ገዢው የፕሬዝደንት ኦማር ገሌ ‘ዩኒየን ፎር ፕሬዚደንሺያል ማጆሪቲ’ ፓርቲ ምርጫውን እንደሚያሸንፍ ከወዲሁ የተረጋገጠ ይመስላል።

ጂቡቲ በአፍሪካ ቀንድ ትንሿ አገር ብትሆንም፣ በቀይ ባህር መግቢያ ላይ እንደመገኘቷ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ ለሚሹ፣ እንዲሁም ወታደራዊ አቅም ያላቸው ኃያላን ሀገራትን ትኩረት ትስባለች፡፡

ከምርጫ ራሱን ያስወገደው ተቃዋሚው ፓርቲ ምርጫው ነጻና ፍትሃዊ አይሆንም ብሏል። የምክር ቤት አባላት ምርጫ የሚካሄደው ከሁለት ዓመት በፊት የተካሄደውንና ኦማር ገሌ 97 በመቶ ድምጽ አግኝተውበት ያሸነፉበትን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ተከትሎ ነው። ገሌ አምስተኛ የሥልጣን ዘመናቸውን ይዘዋል፡፡

“ይህ ምርጫ እንዲሁ ለመደረግ ያህል የሚፈጸም እንጂ፣ ምንም ለውጥ አይኖርም” ብሏል የ 32 ዓመቱ ሥራ አጥ አሊ፡፡

የ75 ዓመቱ ገሌ አገሪቱን ከእ.አ.አ 1999 ጀምሮ ስልጣን ላይ የቆዩ ሲሆን የሚዲያ ነጻነትንና የተቃዋሚዎችን መብት በመሸርሸር ይወቀሳሉ።

በዩክሬን እየተካሄደ ባለው ጦርነት እንዲሁም በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ምክንያት ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ጂቡቲ ኢኮኖሚዋ ክፉኛ ተጎድቶ ነበር። የዓለም የገንዘብ ድርጅት ግን በዚህ ዓመት ኢኮኖሚዋ በአምስት በመቶ ያድጋል ሲል ተንብይዋል።

XS
SM
MD
LG