በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ዋና ጸሃፊ ለአፍሪካ ተጨማሪ የብድር እፎይታ እንዲሰጥ ጠየቁ


የተመድ ዋና ጸሃፊ ለአፍሪካ ተጨማሪ የብድር እፎይታ እንዲሰጥ ጠየቁ
የተመድ ዋና ጸሃፊ ለአፍሪካ ተጨማሪ የብድር እፎይታ እንዲሰጥ ጠየቁ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ የአፍሪካ ሀገራት አስፈላጊውን የብድር እፎይታ እያገኙ እንዳልሆነ ፣በፋይናንስ ድጋፍ እጥረት ምክንያት አህጉሪቱ በከፋ ችግር ውስጥ እንደምትገኝ አስታወቁ ።

የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ከተከፈተ በኃላ አዲስ አበባ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ዋና መስሪያ ቤት በነበረ ጋዜጣዊ ማስገንዘቢያ ላይ ንግግር ያደረጉት ጉቴሬስ የአህጉረ አፍሪካን አቅም ለማሳደግ ፣ ተደራራቢ ተግዳሮቶችን አስቀድሞ መቅረፍ እንደሚገባ ተናግረዋል ።

በቅጡ ግልጋሎት የማይሰጥ እና ፍትሐዊ ያልሆነ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት በርካታ ሀገራት የሚያስፈልጋቸውን የብድር እፎይታ እንደ ነፈገ ያወሱት ዋና ጸሃፊው፣ " ከጤና እና ትምህርት እስከ ማህበረሰብ ጥበቃ፣ስራ ፈጠራ እና የጾታ እኩልነትን የሚመለከቱ ስርዓቶች እና መዋቅሮች መዋለ-ነዋይ እና ድጋፍ ተርበዋል " ብለዋል ።

ጉቴሬስ በትናንቱ የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ መክፈቻ ዝግጅት ላይ በተሰማ ንግግራቸው ብድር በአህጉሪቱ ምጣኔ ሀብታዊ አቅም ላይ ያለውን ተጽዕኖ አመላክተዋል ።የዓለም የመዋለ-ነዋይ አበዳሪዎች የፋይናንስ ዕቅዳቸውን ሲያወጡ ብዙ ጊዜ የአፍሪካ ሀገራትን እንደሚዘነጉ አጽንኦት ሰጥተዋል ።

ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ሀገራት የብድር እፎይታ የሚሰጥ አዲስ የብድር መዋቅር እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG