በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቱርክ ውስጥ ለ296 ሰዓታት በፍርስራሽ ውስጥ የቆዩ የቤተሰብ አባላት በሕይወት ተገኙ 


በቱርክ በፍርስራሽ ውስጥ ለ12 ቀናት ተቀብረው የነበሩ የቤተሰብ አባላት በነፍስ አድን ሰራተኞች ጥረት በሕይወት ተገኝተዋል።
በቱርክ በፍርስራሽ ውስጥ ለ12 ቀናት ተቀብረው የነበሩ የቤተሰብ አባላት በነፍስ አድን ሰራተኞች ጥረት በሕይወት ተገኝተዋል።

የቱርክ እና የሶሪያ ስፍራዎች በርዕደ-መሬት መለኪያ 7.8 በተቆጠረው የመሬት መንቀጥቀጥ ከተመቱ ከ12 ቀናት በኃላ ባል ፣ ሚስት እና አንድ ልጃቸው ከፍርስራሽ ውስጥ በህይወት እንደወጡ የቱርኩ መንግስት የዜና አውታሮች ዘግበዋል ።ይሁንና ከፍርስራሹ ውስጥ የወጣው ህጻን ወደ ሆስፒታል ከተወሰደ በኃላ ህይወቱ እንዳለፈች ተሰምቷል።

ከኪርጊስታን የመጣ የነፍስ አድን ቡድን የ49 ዓመቱ ሳሚር ሞሃመድ አካርን ፣ የ40 ዓመቷ ባለቤታቸው ራግዳን እና የ12 ዓመቱን ልጃቸውን ከደቡብ ቱርኳ አንታኪያ ከተማ ከሚገኝ የመኖሪያ ህንጻ ፍርስራሽ ስር ሊያወጣቸው ችሏል።

ከነፍስ እድን ሰራተኞች መካከል አንዱ ተጨማሪ ህይወታቸው ያለፈ ሁለት ህጻናት መገኘታቸውን አስታውቋል። አናዱሉ የተባለው አውታር ህጻናቶቹ የሳሚር ሞሃመድ እና ራግዳ አካር ልጆች መሆናቸውን ዘግቧል። የሀታይ ግዛት ዋና ከተማ የሆነችውን አንታኪያን የጎበኙት የጤና ሚኒስትር ፋርቲን ኮካ በሙስጠፋ ካማል ሆስፒታል ውስጥ የህክምና ርዳታ እየገኘ የሚገኘው አባት ወደ ቀልቡ እየተመለሰ እንደሆነ አስታውቀዋል።

የሀታይ ግዛት በቱርክ 40,642 በ ሶሪያ 5800 ሰዎችን በጨረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ በእጅጉ ከደቀቁ ስፍራዎች መካከል አንዱ ነው። በህይወት የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት አሰሳው እና ርብርቡ በቱርክ የቀጠለ ሲሆን ፣ የሀገሪቱ የአደጋ ጊዜ ግብረ-መልስ ተቋም ይህ ጥረት በዛሬው ዕለት እንደሚጠናቀቅ አስታውቋል ።

XS
SM
MD
LG