በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን 'እስከመጨረሻው' ለዩክሬን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ገቡ


ፋይል - የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዋይት ኃውስ ንግግር ሲያደርጉ።
ፋይል - የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዋይት ኃውስ ንግግር ሲያደርጉ።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሩሲያ ዩክሬንን የወረረችበትን አንደኛ አመት ለማስታወስ ማክሰኞ እለት በፖላንድ ንግግር ለማድረግ በዝግጅት ላይ ናቸው። ምንም እንኳን የሪፐብሊካኖች እና የአሜሪካውያን ድጋፍ እየላላ ቢመጣም፣ ባይደን በሚያደርጉት ንግግር ጦርነቱ እከሚያበቃበት ጊዜ ዩናይትድ ስቴትስ ዩክሬንን ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋግጣሉ ተብሏል።


ባይደን በዚህ ጉዟቸው ወደ ዩክሬን የመጓዝም ሆነ ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ጋር የመገናኘት እቅድ እንደሌላቸው ዋይት ኃውስ ቢያስታውቅም፣ አንዳንድ ተንታኞች ግን ምናልባት ሁለቱ መሪዎች በፖላንድ ሊገናኙ እንደሚችሉ ገልፀዋል።

ተንታኞች እንደሚሉት ሞስኮ ግጭቱን ወደ ማዳከም ስልት በመቀየር የዩክሬንን ቁርጠኝነት እና የምዕራብ አገሮችን ትዕግስት ለማሟጠጥ እየሞከረች ነው። ዩክሬን የምዕራብ ሀገራት በሚሰጧት የከፍተኛ ቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑ የጦር መሳሪያዎች እየተረዳች ሲሆን፣ ሩሲያ በኢኮኖሚዋ፣ የሰው ኃይሏ እና የመከላከያ መሳሪያዎችን በማምረት አቅሟ እየተጠቀመች ነው።


ሆኖም አንዳንድ ሪፐብሊካን ህግ አውጪዎች አሜሪካ ለኪቭ ደህንነት፣ ኢኮኖሚ እና ሰብዓዊ ርዳታ እያወጣች ያለችው 40 ቢሊየን ዶላር ላይ ጥያቄ ማንሳት ጀምረዋል።


ከህዝብ የተሰበሰበ አስተያየት እንደሚያሳየውም ከአሜሪካ ህዝብ ግማሽ የሚሆነው ዋሽንግተን ኪየቭ በተቻለ ፍጥነት ለሰላም ሀሳብ እንድትገዛ ግፊት ማድረግ አለባት ብለው ያምናሉ።

XS
SM
MD
LG